እግዚአብሔርን ለማገልገል እንጂ ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፡፡ እግዚአብሄርን ማገልገል እንጂ ባለጠጋ ለመሆን መድከም የሚገባው ነገር አይደለም፡፡ ሰውን ማገልገል እንጂ ባለጠጋ ለመሆን መድከም ለእግዚአብሄር ልጅነት ደረጃችን አይመጥንም፡፡
ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል፤ ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡4-5
ሰው የተፈጠረው ባለጠጋ ተደርጎ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ሌላውን ለማገልገል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለሌላው ነው፡፡
ሰው ግን የተፈጠረበትን አላማ ትቶ በራሱ ላይት ብቻ ሲያተኩት ጅይወት ሁሉ ይዛባበታል፡፡ ሰው በነፉግነት በራሱ ጥቅም ላይ ብቻ ሲያተኩር ከእግዚአብሄር ሃሳብ ይወድቃል፡፡ ሰው በራስ ወዳደነት ሰውን ከማገልገል ሲሰስት የህይወቱን አላማ ይስታል፡፡
ሰው ሰውን የፈጠረበትን ማስተዋል ሲተውና በገዛ ማስተዋሉ ሲደገፍ ይሞኛል፡፡ ሰው የተፈጠረበትን የእግዚአብሄን ጥበብ ሲተው ሞኝ ይሆናል፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5
ሰው እግዚአብሄር እንዲተጋ የሰጠውን ሰዎች የማገልገልና የመጥቀም አላማ ሱተው ህይወቱን ያባክናል፡፡
ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡4
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እግዚአብሄር ራሱ ሰውን እንዲንከባከበውና ሰው ሌላውን ሰው እንዲንከባከን ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄር እንደሚንከባከበው ካላመነና ሌላውን መንከባከብ ትቶ ራሱን በራሱ ለመንከባከብ ሲሞክር የእግዚአብሄር የፈጠረበትን አላማ ይስታል፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡31-33
ለአህዛብ ነው እንጂ ለእኛ ለእኛ ሰውን ማገልግል ትተን ባለጠግነትን መከተል ክብራችን አይፈቅደውም፡፡ ለእኛ ሰውን መጥቀም እንጂ ራስን ለመጠቀም መድከም ለእግዚአብሄር ልጅነት ደረጃችን አይመጥንም፡፡ ለአህዛብ እንጂ ለእኛ ሰውን መጥቀምና ማገልግል እንጂ ባለጠጋ ለመሆን መድከም አይገባንም፡፡
ሰው የተፈጠረበትን ሰውን ማገልገልን ሲከተል ባለጠግነት ይከተለዋል ያገኘዋል፡፡ ሰው የተፈጠረበትን ሰውን የማገልገል አላማ ትቶ ባለጠግነትን ከተከተለ ባለጠግነት ይሸሸዋል፡፡
እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል። የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል። ኦሪት ዘዳግም 28፡1-2
ሰው ሌላውን ሰው ባለጠጋ የማድረግ አላማውንና ትቶ በራሱ ላይ ካተኮረ ባለጠግነት ለራስ ወዳድነት ስላልተፈጠረ ባለጠግነት ይሸሸዋል፡፡
ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል፤ ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡4-5
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አገልጋይ #እረፍት #ድካም #ጥረት #ባለጠግነት #በረከት #አላማ #ልፋት #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ውድድር #ፉክክር #ዋጋ
No comments:
Post a Comment