Popular Posts

Follow by Email

Tuesday, August 21, 2018

መንፈስ ድካማችንን


እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡26-27
ለመፀለይ ስናስብ ብዙ ነገሮች ወደ አእምሯችን ይመጣሉ፡፡ በሰው ልብ ብዙ ሃሳብ አለ፡፡እኛ በጊዜው ያተኮርንበት ነገር እግዚአብሄር ያተኮረበት ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ እኛ ሁሉን ስለማናውቅ በጊዜው የፈለግነው ነገር የማያስፈገን ይሆናል፡፡ በጊዜው ያልፈልገነው ወይም የረሳነው ነገር ደግሞ ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን ነገር ይሆናል፡፡ አንዳነዴ ለራሳችን ልንፀልይ ስንፈልግ የእግዚአብሄር መንፈስ ስለሌላ ሰው እንድንፀልይ ይመራናል፡፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ፈፅምን ስለማናውቅ እንደ ማንኛውም ጊዜ በፀሎታችንም ረጋ ብለን የእግዚአብሄርን መንፈስ ምሪት ውጤታማ እንሆናለን፡፡
መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡10-11
1.      ምን እንደምንፀልይ አናውቅም
በፀሎታችን የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የሚያስፈልገን በእግዚአብሄርን ፊት ይምንፀልየውን ማወቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍጥረታችንን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር የሚያስፈልገንና የማያስፈልገንን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን አሁን ሊሆ ያለውን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር አሁን በምን ሊያጠቃን እንዳቀደ አስቀድሞ ያውቃል፡፡ በፀሎታችን የእግዚአብሄርንም መንፈስ ማስቀደም በፀሎታችን እግዚአብሄር ለአሁን በህይወታችን የሚፈልገውን ነገር እንድንፀልይ ያስችልናል፡፡
2.     መቼ እንድምንፀልይ አናውቅም
መቼ መፀለይ እንደሚያስፍልገን ለመረዳት በፀሎታችን በመንፈስ ቅዱስ መመራት ወሳኝ ነው፡፡ አንዳንዴ በፀሎታችን ልንዘገይ ወይም ያለ አግባብ ልንፈጥን እንችላለን፡፡ መንፈስን ስንከተል ጊዜውን የመለየት ድካችንን ያግዘናል፡፡
ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡16-18
3.     እንዴት እንድምንፀልይ አናውቅም
አንዳንዴ አስበን የማናውቅው አይነት የፀሎት አፀለያየን ስንፀልይ ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ ይህ የሰው ሃሳብ ወይም ችሎታ አይደለም፡፡ ይህ የእግዚአብሄር መንፈስ ምሪት ነው፡፡ በምን አይነት የፀሎት ሁኔታ በእግዚአብሄር ፊት መቅረብ እንዳለብን የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ለምሳሌ በፆም መፀለይ እንዳለብን መንፈስ ይመራናል፡፡
እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡26
ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው። የማርቆስ ወንጌል 9፡29
4.     በምን ፀሎት እንድምንፀልይ አናውቅም
·         በልመና
ልመና አንዴ ልመናችንን አስታውቀንብ ከዚያም በኋላ ስለተደረገልን ነገር እግዚአብሄርን የምናመሰግንበት የፀሎት አይነት ነው፡፡
አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው። የማቴዎስ ወንጌል 21፡22
·         በምልጃ
ምልጃ መንፈስ ቅዱስን በመከተል በሌላ ሰው ፋንታ ወይም በራሳችሁ ህይወት ስለማታውቁት ነገር መቃተት ነው፡፡ ምልጃ ደግማችሁ ደጋግማችሁ የምታሳስቡት እንጂ እንደልመና እንዴ ብቻ ለምናችሁ የምታመሰግኑበት የፀሎት አይነት አይደለም፡፡
·         በምስጋና
አንዳንዴ የሚያስፈልገንም መለመን ሳይሆን ማመስገን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደ ምስጋና ከመራን የፀሎት ጥያቄያችን በምስጋናችን ይመለሳል፡፡
በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡19-20
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፦ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉትንም፥ ጌጠኛ ልብስም ለብሰው የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ። ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ተመቱ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 2021
·         በውጊያ
በየትኛው የህይወት አቅጣጫችን የሰይጣን ስራ እያጠቃን እንደሆነ መንፈስ ካላሳየን በስተቀር ፀሎትን ሁሉ የውጊያ ፀሎት ማደረግ ወይም ልመና ብቻ ማድርግ ትክክል አይሆንም፡፡ አንዳንዱ ነገር የሚፈታው ሰይጣን የያዘውን በልጅነት ስልጣን ስናስለቅቅ ብቻ ነው፡፡
እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር። ይህንም እጅግ ቀን አደረገች። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ። የሐዋርያት ሥራ 16፡17-18
·         በአምልኮ
ስለአንዳንዱ የህይወት ጥያቄያችን እርሱን እንዳይ ብቻ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። ኦሪት ዘጸአት 23፡25
5.     ለምን ያህል ጊዜ እንደምንፀልይ አናውቅም
እንዲሁም ፀልየን ልባችን ሲያርፍ ፣ ሰላም ሲሰማንና ሸክማችን ከእኛ ላይ ቀለል ሲል የእግዚአብሄር መንፈስ እንደመራን እናውቃለን፡፡ የፀሎት የመጀመሪያውን ጊዜ መንፈስ ሊመራን እንደሚገባው ሁሉ ፀሎታችንን ጨርሰን ወደሌላ ነገር ማለፍ እንዳለብን የሚመራን መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
በእርጋታ ምሪቱን እየፈለግን መንፈስን ከተከተልን ፍሬያማ የፀሎት ህይወት ይኖረናል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #ይማልዳል #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል

No comments:

Post a Comment