Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, August 8, 2018

ባላገር አይደለንም

ይህ አለም አገራችን አይደለም፡፡ አገራችን ከሰማይ ነው፡፡ ተላላፊዎች ነን፡፡ ጊዜያዊ ጎብኚዎች ነን፡፡ የአገራችን የሰማይ አገር መልክተኞች ነን፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡20
በምድር ላይ የምንኖረው እንደ እንግዳ ነው ፡፡
እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። ወደ ዕብራውያን 11፡13
የሚበልጥ ከተማ ተዘጋጅቶልናል፡፡
አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡16
በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡  
በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡19
ምንጫችን ከዚህ አይደለም
ሰው የመንፈሱ መኖሪያ ቤት ስጋው ከምድር አፈር እንጂ እንጂ ሰው ስጋ አይደለም፡፡ መኖሪያ ስጋው እንጂ ሰው ከምድር አይደለም፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡  
እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው። ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም። የዮሐንስ ወንጌል 17፡14-16
ጌታችን ከዚህ አይደለም
የእኛ ጌታ የምንኖርለት የምንታዘዘው ጌታ በምድር የለም፡፡ የምንገዛለትና የምንሰማው ጌታ በአይን አይታይም፡፡ የምንከተለው ጌታ በመንፈስ በልባችን ይኖራል፡፡
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡15
የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡6-7
መንግስታችን ከዚህ አይደለችም
እኛን የሚገዛን መንግስት የሰማይ መንግስት ነው፡፡ እኛ  የምንገዛለት መንግስት እግዚአብሄር ንጉሱ የሆነበት የእግዚአብሄር መንግስት ነው፡፡  
ኢየሱስም መልሶ፦ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 18፡36
መንግስታችን በአይን የሚታይ ምድራዊ መንግስት አይደለም፡፡ መንግስታችን በመወለድ የሚገባበት በመካከላችን ያለች የምትገዛ መንግስት ነች፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። የዮሐንስ ወንጌል 18፡3፣5
አገራችን ከዚህ አይደለም
በምድር ላይ እንግዶች ነን፡፡ ይህ ምድር የመጨረሻ ቤታችን አይደለም፡፡ ከሞት በኋላ የዘላም ህይወት አለን፡፡
እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡20
እንደ አለማዊያን እዚሁ ኖረን እዚሁ እንድምንቀር አድርገን አንኖርም፡፡ ሰው ከሞተ በኋላ ለፍርድ ከሞት ይነሳል፡፡  
ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡32
ህጋችን ከዚህ አለም አይደለም
ሰዎች በምድር ላይ በከንቱ በሚፎካከሩበት የምድር ህግ አንመራም፡፡ የአለም ሰዎች ከሚወዳደሩበት ከንቱ ውድድር እና ፉክክር ራሳችንን እናገላለን፡፡
በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ። የያዕቆብ መልእክት 2፡12
የእግዚአብሄር ፈቃድ እንጂ የአለም ምኞት እንደሚገዛቸው ሰዎች የአለም ስርአት አይገዛንም፡፡
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡15-16
እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡8
መንፈሳችን ከዚህ አይደለም
እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡12
ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡11
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ትዳር #ንግድ #ወታደር #ዘማች #መዋረድ #መከራ #ፈተና #መፅናት #መታገስ #እንግዶች #መጻተኞች #ምስኪኖች #ተስፋ #አለም #የተገባ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment