Popular Posts

Follow by Email

Friday, August 3, 2018

የእውነት ዓምድና መሠረት

ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡15
ቤተክርስትያን የእውነት ጠበቃ ነች፡፡ የእግዚአብሄር ቤት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን የእውነት መገኛ ነች፡፡ የትም እውነት ባይገኝ በቤተክርስትያን እውነት መገኘት አለበት፡፡ ቤተክርስተያን የእውነት ማጣቀሻ ነች፡፡ ቤተክርስትያን የእውነት ምስክር ነች፡፡
የቤተክርስተያን ሁለንተናዋ እውነት ነው፡፡ ቤተክርስትያን በውሸት አትሰራም፡፡ ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በእውነት እና በእውነት ላይ ብቻ ነው፡፡ ቤተክርስተያን የቆመችው እና የተገነባችው በእውነት ነው፡፡ የቤተክርስትያን ጣራና ግድግዳ እውነት ነው፡፡ የቤተክርስተያን አምድ እና መሰረት እውነት ነው፡፡ ከቤተክርስትያን ውስጥ እውነትን ካወጣን ቤተክርስትያን ምንም አይቀራትም፡፡ በቤተክርስትያን ምንም ነገር ቢታጣ እወነት ግን አይታጣም፡፡  
ቤተክርስትያን ስለ እውነት ልመሰክር መጥቻለሁ ባለው በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ ነች፡፡
ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው። የዮሐንስ ወንጌል 18፡37
ቤተክርስትያን የእውነት ቃል በሆነ በእግዚአብሄር ቃል የምትመራ እና የተቀደሰች ህብረት ነች፡፡
በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 17፡17
ቤተክርስትያን እኔ እውነት ነኝ ባለው በኢየሱስ ላይ የተመሰረተች የክርስቶስ አካል ነች፡፡
ቤተክርስትያን የውሸት አባትን የዲያቢሎስን ስራ ለማፍረስ በምድር ላይ ያለች የእውነት መልክተኛ ነች፡፡  
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44
ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡9
ቤተክርስትያን በጠላት ሃይል ላይ ያላት አንዱ የጦር መሳርያ እውነት ነው፡፡ ቤተክርስትያን እውነት ከሌላት የመዋጊያና የማሸነፊያ የጦር መሳሪያ አይኖራትም፡፡
እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡14-15
ቤተክርስትያን እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ የተባሉ ሰዎች ስብስብ ነች፡፡
ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡24-25
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስቲያን #አምድ #መሰረት #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment