Popular Posts

Monday, August 13, 2018

የማእረጎች ሁሉ ማእረግ

እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። የማቴዎስ ወንጌል 23፡7-10
ሰዎች በምድር ላይ ማደግና መለወጥ ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ መከበር በማንነታቸው አንቱ መባልን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ እከሌ መባልን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ማእረግ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፡፡
በምድር ላይ ብዙ አይነት ማእረጎች አሉ፡፡ በምድር ላይ የመንግስት ማእረግ አለ፡፡ በምድር ላይ የወታደርነት ማእረግ አለ፡፡ በምድር ላይ የመስሪያቤት የተለያየ ማእረግ አለ፡፡ ሰዎች በዚያ የማእርግ ከፍተኛ ቦታ ላይ መድረስ ይፈልጋሉ፡፡
የሰው የማደግ የመለወጥ ፍሎጎት ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡
በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ ሁለት ማእረግ አለ፡፡ አንደኛው ማእረግ የጌታ የእግዚአብሄር ማእረግ ሲሆን ሌላው ማእረግ ደግሞ የልጅነትና የተከታይነት ማእረግ ነው፡፡
ሰዎች ከዚህ ከልጅነት ማእረግ በላይ ምንም አይነት ማእረግ መፈልግ የለባቸውም፡፡ ሰዎች የስህተት ማእረግ ለራሳቸው ይሰጣሉ እንጂ ከዚህ ከልጅነት የተሻለ ማእረግ የለም፡፡ ከዚህ ከልጅነት ማእረግ በላይ ማእረግ የሚፈልግ ሰው ራሱንም ሌሎችን ያስጨንቃል፡፡
ኢየሱስ ፈሪሳዊያንን ሲገስፅ እንደዚህ ብሎ ነበር፡፡
በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። የማቴዎስ ወንጌል 23፡6-10
ማንም ክርስትያን ከልጅነት አድጎ አባት አይሆንም፡፡ ክርስትያን ሁሉ የእግዚአብሄር ልጅ ነው፡፡
የልጅነት ስም ያልበቃው ሰው ከልጅነት በላይ የሌለውን ማእረግ ለማግኘት ሲወጣና ሲገባ ህይወቱን በከንቱ ያባክናል፡፡
አሁን የሚያስፈልገን ልጅነታችንን ማጥናትና በልጅነት መብታችን መጠቀም እንጂ ከልጅነትና ከወንድምነት በላይ የሆነ ማእረግ መፈለግ አይደለም፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ማእረግ #ልጅነት #ብርሃን #ስልጣን #አባት #ጌታክርስቶስ #ወንድማማች #ሊቃውንት #ስራ #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለጠግነትምቾት #አቅርቦት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment