Popular Posts

Saturday, August 18, 2018

መንፈስ ከእግዚአብሄር መሆኑን የምንለይበት ሁለቱ መንገዶች

ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና። የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ። 1 የዮሐንስ መልእክት 4፡1-3
መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሄር መንፈስ አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ አለ እርኩስ መንፈስ አለ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ አለ የሰይጣን መንፈስ አለ፡፡
መንፈስ ሁሉ የሰይጣን ከመሰለን እንደምንሳሳት ሁሉ መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሄር ከመሰለን ደግሞ እንሳሳታለን፡፡
የመንፈስን እንቅስቃሴ አለመናቅ ነገር ገን መፈተን ትይገባል፡፡ የመንፈስን እንቅስቃሴ ፈትነን የመጣልና የመቀበል ሃላፊነት ያለብን እኛ ላይ ነው፡፡ የምንፈስን እንቅስቃሴ እንድንቀበል የሚያስገድደን ሰው የለም፡፡
የእግዚአብሄርን መንፈስ እንቅስቃሴ ለመለየትና በእግዚአብሄር አሰራር ተጠቃሚ ለመሆን መንፈስን የምንልይበትን መንገድ ማወቅ ይገባናል፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ ስንለይ የሰይጣንን መንፈስ አሰራር ከህይወታችን መቃወም እንችላለን፡፡
1.      ክርስቶስ በስጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ

ሰይጣን የሰዎችን መዳን አይፈልግም፡፡ ክርስቶስ በስጋ መጥቶ የሃጢያቱን እዳ በመስቀል ላይ እንደከፈለለት ሰው ካላመነ አይድንም፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡2-3

2.     ክብሩን ከክርስቶስ የሚወስድ መንፈስ

የእግዚአብሄርን መንፈስ ከክፉ መንፈስ የሚለይበት ሌላው መንገድ የእግዚአብሄ መንፈስ በነገር ሁሉ ክርስቶስን ሲያከብት የሰይጣን መንፈስ ክብሩን ከክርስቶስ ይመልሳል፡፡ ሰይጣን ከርስቶስ ክብሩን አይውሰድ አንጂ ማንም ክብሩን ቢወስድ ግድ የለውም፡፡ ሰይጣን የሚፈልገው ከርስቶስ ክብሩን እንዳይወስድ ብቻ ነው፡፡ ክርስቶስ ክብሩን ካልወሰደ ሰይጣን አላማው ይሳካል፡፡

ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ። ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር። ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር። የሐዋርያት ሥራ 89-11

ምንም ያህል ታላላቅ ነገርት ቢያደርግ ክብሩን ለእግዚአብሄር የማያመጣ ከሆነ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡  
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሔርመንፈስ #እርኩስመንፈስ #ሰይጣን #ፈትኑ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነቢያት #ነቢይ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment