Popular Posts

Wednesday, August 15, 2018

ሰው በኃይሉ አይበረታምና

እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 29
ሰው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው የተፈጠረው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር ላይ እየተደገፈ እንዲኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር እንዲታመን ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን እንዲከተል ነው፡፡
የእግዚአብሄርና የሰው ግንኙነት እንዲሰምር ሰው ምን ማድረግ እንዳለበትና ምን ማድረግ እንደሌለበት እግዚአብሄር አዝዞት ነበር፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ላይ በተደገፈና የታዘዘውን ነገር ባደረገ ጊዜ ሁሉ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው ግንኙነት የተከናወነ ነበር፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ነፃ መሆን ሲፈልግና ሰይጣንን ሲሰማ በእግዚአብሄር ላይ በማመፁ ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ተበላሸ፡፡  
ሰው በራሱ ሃይል የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ሃይልና እርዳታ ህይወቱን እንዲኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን በማመንና በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ እንዲኖር ነው፡፡ ሰው እምነቱ ከጠፋ ሰው በምድር ላይ የተፈጠረነት አላማ ይጠፋል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6
ሰው በእግዚአብሄር ላይ መደገፍን ሲያቆም ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የግንኙነት ህይወቱ ይቆማል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ላይ መደገፍን ሲያቆም የእግዚአብሄር እርዳታ ከህይወቱ ይቆማል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ላይ ማደገፍ ሲያቆም የህይወት ሃይሉ ይጠፋል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር አሰራር ላይ መደገፍ ሲያቆም እውነተኛ ህይወቱ ይሞታል፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡16-17
ሰው በጉልበቱ አይበረታም
ሰው በራሱ ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልም፡፡ ሰው በራሱ ነገሮችን ለማድርግ ሊሞክር ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን የሚፈልገውን ነገር በህይወታችን ለማድረግ እግዚአብሄር ያስፈልገናል፡፡ ሰው በራሱ ሃይል አይበረታም፡
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና የዮሐንስ ወንጌል 15፡5
ሰው በፀሎቱ አይበረታም
ሰው ካለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ መፀለይና ፍሬያማ መሆን አይችልም፡፡
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡26
ሰው በጥበቡ አይበረታም
ሰው በእግዚአብሄር ጥበብ ካልታመነ በስተቀር የሰው ጥበብ የትም አያደርሰውም፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5
ሰው በበጎነቱ አይበረታም
አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ። እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙረ ዳዊት 16፡1-2
ሰው በሃይሉ አይበረታም
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡29-31
እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፥9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አምላክ #እርዳታ #መንፈስቅዱስ #እምነት #መደገፍ #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መደገፍ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment