Popular Posts

Monday, August 6, 2018

የአንደኝነት ፍላጎት

ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶ፦ ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው። የማርቆስ ወንጌል 9፡35
በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤ የማቴዎስ ወንጌል 20፡26-27
ኢየሱስ ከእናንተ ማንም ታላቅ ሊሆን የሚወድ ንስሃ ይግባ አላለም፡፡ ኢየሱስ ከእናንት ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ ቢኖር ተሳስቷል አላለም፡፡
የአንደኝነት ፍላጎት ትክክል ነው
ሰው አንደኛ የመሆን የመፎካከር ነገር በውስጡ አለ፡፡ ሰው ማሸነፍ በውስጡ ያለ ፍጥረት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለተግዳሮት ነው፡፡ ኢየሱስ እንኳን ስለእግዚአብሄር መንግስት ሲናገር ተግዳሮት ያለባተነ እንድመርጥ ያስተምራል፡፡
በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።  የማቴዎስ ወንጌል 7፡13-14
ሰው አንደኛ ለመሆን ያለው ጥማቱ መከልከል የለበትም፡፡ አንደኛ የመሆን ጥማቱን መከልከል ጎርፍን ለማቆም እንደመሞከር አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰው አንደኛ የመሆን ፍላጎቱ መበረታታት አለበት፡፡
ነገር ግን ደግሞ አንደኛ መሆን ማለት ምን አነደሆነ መማር ደግሞ አለበት፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን መንግስት መርህ መማር አለከበር፡፡ የእግዚአብሄር መንግስትና የአለም መርሆዎች ይላያሉ፡፡ በአለም መንግስት የሚሰራው በእግዚአብሄ መንግስት ላይሰራ ይችላል፡ሸ
በአለም አንደኛነት በተጠቃሚነት መጠን ነው፡፡ ሰው አንደኛ ነኝ የሚለው በሌሎች ሰዎች የሚጠቀመውን ጥቅም አይቶ ነው፡፡ በአልም አንደኛ መሆን ተጠቃሚነት እድለፅነት ነው፡፡ የአለም አንደኝነት ራስ ወዳድንት ንፉግበት ላየ ነው፡ዐ፡
ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። የማቴዎስ ወንጌል 20፡25
በእግዚአብሄር መንግስት ግን አንደኝነት በተጠቃሚነት ብዛት ሳይሆን በጠቃሚነት ብዛት ነው፡፡ በእግዚአብሄ መንግስት ሰው የሚወዳደረው በሚጠቀመው ጥቅም ብዛት ሳይትሆን በሚጠቅመው ጠቃሚነት ብዛት ነው፡፡ በእግዚአብሀር መንግስር ሰው የሚወዳደረው በሚጠቅሙት ሰዎች ብዛት ሳይሆን በሚጠቅማቸው ሰዎች ብዛት ነው፡፡ በእግዚአብሄ መንግስት ያለው የአንደኝነት ውድድር እራሱ በሚገለገልበት የአገልግሎት ጥራት ሳይሆን ሌሎቹን በሚያገለግለው የአገልገሎት ጥራት ነው፡፡
ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ 1 ወደ ጢሞቴዎስ 3፡1-2
በመፅሃፍ ቅዱስ ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ ፍላጎቱ ትክክል አይደለም አላለም፡፡ እንዲያውም መፅሃፍ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶስነትን መፈለግን ያበረታታል፡፡ ሰው በኤጲስ ቆጶስነት የእግዚአብሄርን ህዝብ ማገልገል የመፈለግ ምኞቱ መልካም ምኞት ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ የቤተክርስትያን መሪነትን አገልግሎት የሚፈልግ ሰው ምን ምን ማሟላት እንዳለበት ያስተምራል እንጂ የቤተክርስተያን አጋልጋይነትን ምኞት አይቃወምም፡፡ ቤተክርስትያን አገልጋይን ትጠራለች፡፡ ሰው አገልገሎትን ፈልጎ ሲመጣ በእንዴት ያለ ባህሪ እና የህይወት ዘይቤ ጌታን እና የእግዚአብሄር ህዝብን እንደሚያገልግል መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል እንጂ የመሪነትን ፍላጎት አይቃወምም፡፡
የቤተክርስትያን መሪ ሰዎችን ለማገልገል እና ለመጥቀም ምን ባህሪ እንደሚያስፈልጉት ያስተምራል እንጂ አገልጋይነትን አይቃወምም፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ የተጠቃሚነትንና በሰዎች የመገልግለን ፍላጎት አያበረታም እንጂ የጠቃሚነትንና የአገልጋይነት ፍላጎት ያበረታታል፡፡ በፍቅር ላይ የሚሰራ ህግ እንደሌለ ሁሉ በማገልገል ላይ የሚሰራ ህግ የለም፡፡ ማገልገልን ፣ በማገልገለ መበላለጥን ፣ በማገልገል መወዳደርን የሚቃወም ህግ የለም፡፡
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22-23
በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤ የማቴዎስ ወንጌል 20፡26-27
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment