ስለሰው
ስናስብ የሰው ዋጋ በምን ይለካል የሚለው ጥያቄ ወደ አእምሮዋችን ይመጣል፡፡ የሰው ዋጋ በምን ይለካል ብለን የምንጠይቀው የራሳችንን
ዋጋ ለማወቅና ዋጋችንን ከፍ ለማድረግ ስለምንፈልግ ነው፡፡ የሰው ዋጋ በምን ይለካል ብለን የምንጠይቀው የራሳችንን ዋጋ ለማወቅና
ከዋጋችን በታች ላለመኖር ስለምንፈልግ ነው፡፡ የሰው ዋጋ በምን ይለካል ብለን የምንጠይቀው ሰውን እንደዋጋው ለመያዝ ስለምንፈልግ
ነው፡፡ የሰው ዋጋ በምን ይለካል ብለን የምንጠይቀው በዋጋ አሰጣጣችን እንዳንሳሳት ስለምንፈልግ ነው፡፡
ሰው
እጅግ ውድ ፍጥረት ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረ ፍጡር ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ክብር የተፈጠረ ፍጡር
ነው፡፡ ሰው ራሱን የሚይዝበት አያያዝ ራሱን ሊያከብረውና ሊያዋርደው ይችላል፡፡
የሰው
ክቡር መሆኑን ካላወቀ ከደረጃ በታች ሊኖር ይችላል፡፡
ሰው
ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። መዝሙረ ዳዊት 49:12
ሰው ክቡር መሆኑን ካላወቀ ራሱን ሊያዋርድ ይችላል፡፡
ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡24-25፣28
ሰው
የተፈጠረው ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዲቀበልና እግዚአብሄርንና
ሰውን እንዲወድ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርንና ሰውን ካልወደድ የተፈጠረበትን አላማ ይስታል ህይወቱም ትርጉም የለሽ ይሆናል፡፡
አንተም
በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች
ናት። ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ
የለችም። የማርቆስ ወንጌል 12፡30-31
ሰው
የእግዚአብሄርን መልክ ፍቅርን ሲያጣ ማንነቱን ያጣል፡፡ ሰውን ክቡር የሚያደርገውን ፍቅርን ካጣው ከንቱ ይሆናል፡፡
በሰዎችና
በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም
ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ
ሰዎች 13፡1-2
ሰው
የተፈጠረበትን አላም ፍቅርን ከሳተው የህይወት አላማውን ይስታል፡፡
የትእዛዝ
ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡5
የሰው
ሃብቱና ሞገሱ በፍቅር መኖር ነው፡፡ ሰው በፍቅር ለመኖር ዲዛይን ስለተደረገ ሰው ፍቅርንና ህይወትን ሲጥል የህይወት ንድፉን በመጣል
በሞት ይኖራል፡፡
እኛ
ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። 1ኛ የዮሐንስ
መልእክት 3፡14
ፍቅር
ማለት በመረዳት ራስን ከሌላው ጋር ማስተባበር ነው፡፡ ፍቅር ማለት ለሌላው መልካም ማሰብ ፣ መልካም መናገርና መልካም ማድረግ ነው፡፡
የሰውን
ዋጋ ከፍ የሚያደርገው በልቡ ያለው ፍቅር ነው፡፡ ምንም ቢሆን ፍቅር ያለው ሰው ይከበራል፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ምንም ቢኖረው በእርሱ
ያላችሁ መተማመን ይቀንሳል፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ማንም ቢሆን ማንነቱ ይቀልባችኋል፡፡
በሰዎችና
በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም
ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ
ሰዎች 13፡1-2
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ
#ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ከንቱ #ምንም #ምሪት #ድምፅ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment