Popular Posts

Friday, August 3, 2018

ያልተሰራ የእግዚአብሔር ቤት

እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1 የጴጥሮስ መልእክት 2፡5
እግዚአብሄር ሰው የፈጠረው ከሰው ጋር ህብረትን ለማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ከሰው ጋር በሚገባ መግባባት እንዲችል ነው፡፡
እግዚአብሄር በምድር የሚኖረው በሰው ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ የሚያድረው በሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር የሚገለጠው በሰው ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ በስፋት መገለጥ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ መታወቅ ይፈልጋል፡፡
ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡19-20
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚናገርበት ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚኖርበት ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚያርፍበት ሰው ይፈልጋል፡፡
ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።የዮሐንስ ወንጌል 14፡23
እግዚአብሄር በህይወታችን በስፋት እንዲኖር ፣ ሰዎችን እንዲነካና እንዲደርስ ለእግዚአብሄር መኖሪያ ሆነን በስፋት መሰራት አለብን፡፡ ለእግዚአብሄር መኖሪያ ሆነን በተገነባን መጠን እግዚአብሄር በስፋት በውስጣችን ይገለጣል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሰምተን ባልታዘዝንና ባላደግን ቁጥር እግዚአብሄር በስፋት ሊኖርብን ፣ ሊያርፍብን ፣ ሊናገርብንና ሊመላለስብን አይችልም፡፡  
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2
ሰው የተሰራ ፣ ሰፊና የተመቻቸ ቤት እንደሚፈልግ ሁሉ እግዚአብሄር በምድር ላይ ለማረፍ ፣ ለመኖር ፣ ለመናገርና ለመስራት በቃሉ የተለወጠ የእግዚአበሄርን ቃል የሚታዘዝ በቃሉ ያደገ እግዚአብሄርን የሚያመልክ ህይወት ይፈልጋል፡፡ ሰው ያልተሰራ ቤት እንደማይመቸው ሁሉ እግዚአብሄርም ያልተሰራ ቤት እንደልቡ ለማረፍ ፣ ለመውጣት ፣ ለመሄድና ለመስራት አይመቸውም፡፡
በእግዚአብሄር ቃል በተሰራንና ባደግን መጠን እግዚአብሄር በስፋት ያርፍብናል ፣ ይኖርብናል እና ይናገርብናል፡፡
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡5
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ትህትና #የእግዚአብሔርቤት #በቃሉመንቀጥቀጥ #ማረፊያ #መኖሪያ #የተሰበረልብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ማደሪያ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ

No comments:

Post a Comment