Popular Posts

Follow by Email

Friday, August 10, 2018

የገሃነም ደጆችም የማይችሉአት ቤተክርስትያን ምልክቶች

እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።  የማቴዎስ ወንጌል 16፡18
ቤተክርስትያን የጌታን ስራ ለመስራት ከአለም የተጠሩ የቅዱሳን ስብስብ ነች፡፡ እውነተኛዋን ቤተክርስትያን ምልክቶች ካወቅን ከቤተክርስተያን ጋር ሙሉ ለሙሉ በመተባበር የእግዚአብሄርን ሃሳብ በራሳችን ዘመን አገልገለን ማለፍ እንችላል፡፡
ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤ የሐዋርያት ሥራ 13፡13
በምንም ነገር ውስጥ ብታልፍ የገሃነም ደጆችም የማይችሉአትና የእግዚአብሄርን ፈቃድ በምድር አስፈፅማ የምታለፍን ቤተክርስቲያን ምልክቶችን ከመፅሃፍ ቅዱስ እንመልከት
1.      የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የመጨረሻ ስልጣንዋ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የምትመራው በመፅሃፍ ቅዱስ መርሆዎች ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የእግዚአብሄር ቃል የአስተሳሰብ የንግግርና የድርጊት መመሪያዋ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ማንኛውንም ሃሳብ ፣ ንግግርና ድርጊት የምትመዝነው በእግዚአብሄር ቃል መመዘኛ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የማይስማማ ማንኛውንም ሃሳብ ማሰብ መናገርና ማድረግ አትፈልግም፡፡
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡8
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የማይሄድን ንግግር አትናገርም፡፡ እውነተኛዋ የክርስቶስ ቤተክርስትያን ንንግርዋ ሁሉ ከእግዚአብሄር ቃል ሃሳብ ጋር የሚሄድ ብቻ ነው፡፡  
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡11
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን መፅሃፍ ቅዱስ ያላለውን ማንኛውንም ነገር ላለማድረግ ትጠነቀቃለች የእግዚአብሄር ቃል ያለውን ለማድረግ ግን ትተጋለች ዋጋም ትከፍላለች፡፡
የእግዚአብሄር ቃል የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የመጨረሻው ባለስልጣን ነው፡፡
2.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው በሚለው መገለጥ ላይ ነው፡፡

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በሰዎች አስተምሮት ላይ አይደለም፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅነት መገለጥ ላይ ነው፡፡

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ስለሆነ እርሱን እንደ አዳኝ የተቀበልን ሁላችን የእግዚአብሄር ልጆችና የእርሱ ቤተሰብ እንደምንሆን ባለው መገለጥ ላይ ተመስርታለች፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው የእግዚአብሄር ልጅነትና የእግዚአብሄር ቤተሰብነት የክብር መገለጥ ላይ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በእግዚአብሄር አባትነትና በእኛ ልጅነት ግንኙነት መገለጥ ላይ ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። የዮሐንስ ወንጌል 1፡12-13

እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡31-32

3.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በወንጌል በአላማ ላይ ነው፡፡
ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት? መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6፡10
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን በምድር ላይ ለምን አላማ እንዳለች ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተወሰነችው የተጠራችበትን የወንጌልን የመስበክ የታላቁ ተልእኮ ስራ ላይ ነው እንጂ ያልተጠራችበት ሌላ ነገር ላይ አይደለምን፡፡
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። የማቴዎስ ወንጌል 28፡19-20
4.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በትንሳኤ ትምህርት ላይ ነው
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ላይ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው እኛም እርሱን የምንከተል ከእርሱ ጋር ሞተን በመነሳታችን የመገለጥ እውቀት ላይ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተመሰረተችው በቃል ብልጫ ሳይሆን መንፈስንና የትንሳኤን ሃይልን በመግለጥ ነው፡፡ 
እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡1-2
5.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን አጥቂ እንጂ ተከላካይ ብቻ አይደለችም

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የተሰጣትን የወንጌል መልእክት ለማዳረስ ወጥታ የምትመሰክር ወንጌልን በሃይልና በስልጣን የምትሰብክ ቤተክርስትያን ነች፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ራስዋን በመከላለክ ላይ ብቻ የተጠመደች ህብረት አይደለችም፡፡ እውነተኛዋ ቤተክርስትያን ተቋቁሞ በማለፍ የምትወሰን ብቻ ሳትሆን አለማዋን ለማስፈፀም በሃይል ትወጣለች፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የውስጥዋን ችግር በመፍታት የተጠመደችና ወንጌልን ለመስበክ ጊዜ የሌላት ህብረት አይደለችም፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የውስጥዋን ችግር ተወት አድርጋ  ለእግዚአብሄር አደራ ሰጥታ ጭንቀትዋን በእግዚአብሄር ላይ ጥላ ወጥታ ሰዎችን ከጠላት ግዛት የምትናጠቅ ህብረት ነች፡፡

አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። የይሁዳ መልእክት 1፡22-23

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የወንጌል ማህበርተኛ ለመሆን የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ተዘጋጅታለች፡፡

ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ። በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡22-23

6.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን በሰው ትምህርት ላይ አልተመሰረተችም፡፡

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስቲያን ስርና መሰረትዋ በጌታ የታነፀ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን በእግዚአብሄር ቃል እውቀት የበሰለች ከመሆንዋ የተነሳ የትምህርት ነፋስ አያፍገመግማትም፡፡

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14

7.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የምትሻው የላይኛውን ነው
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ምድራዊዉን ነገር ለመጠቀሚያነት እንጂ ምድራዊ ሃብትና ንብረት ላይ አታተኩርም፡፡
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡1-2
መፅሃፍ ቅዱስ አስቀድማችሁ የእግዚአብሄር ፅድቅና መንግስቱን ፈልጉ እንደሚል የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የምትፈልገው የእግዚአብሄርን ጽፅድቅና መንግስቱን ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን እግዚአብሄር ስለሚያሟላው ስለምድራዊ ፍላጎት አትወጣም አትገባም፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስትን ስትፈልግ ሁሉ ነገር እንደሚጨርላት በማመን በእረፍት ጌታን ታገለግላች፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡33
የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስቲያን የምታተኩረው የእግዚአብሄር ቤት ሆኖ በሚሰራው የሰው ልጅ ላይ ነው፡፡

እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡5

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ቅድሚያ ሰጥታ የምታንፀው የእግዚአብሄር መኖሪያ የሆነውን ሰማያዊ ህንፃን ነው፡፡

8.     ራሳቸውን የሰጡ ያላቸውን ለመስጠት ለማካፈል ራስዋን የሰጠች ነች
ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡26
አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8፡5
9.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ስልጣንዋን የምታውቅና የምትጠቀም ህብረት ነች

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡20-23

10.    የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ለአክሊል የምትሰራ ህብረት ነች

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን በሰማይ ሃብትን የምታከማች ይምድሩን ሃብት ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም በማዋል የሰማዩን ሃብት የምታከማች ህብረት ነች፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን ከምድር ሃብት ዝና ሽልማት ያለፈ የሰማዩን ሃብትና ዝና ሽልማት ለማግኘዐይት የምትተጋ የእምነት ሰራዊት ነች፡፡

በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡24-25

11.     የገሃነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስትያን የእምነት ሰራዊት ነች

መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡7
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡12
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስቲያን #ህብረት #አምድ #መሰረት #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment