Popular Posts

Follow by Email

Monday, August 27, 2018

የራሴ ነገር ስለሌለኝ አጣዋለሁ ብዬ የምፈራው ነገር የለም

እኛ ራሳችንን አልፈጠርንም፡፡ እግዚአብሄር ግን ለክብሩ ፍጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር ምድርን ከፈጠረ በኋላ እንድናስተዳደር ሃላፊነት ሰጥቶናል፡፡ ምድር የእኛ አይደለችም፡፡ ምድር የእግዚአብሄር ነች፡፡
ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። የዮሐንስ ወንጌል 1፡3
እግዚአብሄር ለአላማው የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ሰጥቶናል፡፡ ያለን ነገር ሁሉ የእግዚአብሄር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ያልሆነ የእኛ የሆነ ነገር የለም፡፡
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡7
እኛ የእግዚአብሄር ነገር ባለቤቶች አይደለንም፡፡ እኛ የእግዚአብሄርን ነገር እግዚአብሄር እንደፈለገው የምናስተዳድር ባለ አደራ አስተዳዳሪዎች ነን፡፡
ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። መዝሙረ ዳዊት 24፡1
ሁሉም ነገር የመጣው ከእግዚአብሄር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሁሉ ነገር የእርሱ ነው፡፡ የሁሉም ሃብትና መልካምነት ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን ለመስጠት በእጅህ ነው። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29፡12
ስለዚህ ነው ሰው የሚያደርገውን ነገር ነገር ሁሉ ስለራሱ ብሎ ሳይሆን ስለጌታ ብሎ ማድረግ ያለበት፡፡
ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡23-24
በመጨረሻ የሰጠንን ሰርተንበትና አትርፈንበት እንዳስረክው የሚጠብቅብን እና የሚቆጣጠረን ባለ አደራ ስለሆንን ነው፡፡  
ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፦ ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። የማቴዎስ ወንጌል 25፡19-21
የእግዚአብሄርን አደራ ባለቤት እንዳለው እንደሌላ ሰው ገንዘብ ባለቤቱ ለሚፈልግለት አላማ ብቻ ማዋል ይገባናል፡፡
እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል? በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል? የሉቃስ ወንጌል 16፡11-12
እኛ የእግዚአብሄር የሆነውን ነገር ሁሉ በልቡና በነፍሱ እንዳለ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ የምናስተዳደር አስተዳዳሪዎች ነን፡፡
ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡10
በህይወት ነፃነትን የሚሰጠው ነገር እኛ የእግዚአብሄር ደጋግ መጋቢዎች መሆናችንን ማወቅ ነው፡፡
ከሁሉም በላይ እኛ የእግዚአብሄር ነገር ደጋግ መጋቢዎች እንጂ ባለቤቶች እንዳልሆንን የራሳችን ነገር እንደሌለን ባወቅን የመሰለ የሚያሳርፍ ነገር የለም፡፡ ሰውን ከጭንቀት የሚገላግለው ሰው ያለው ነገር የእግዚአብሄር መሆኑን ሲረዳ ብቻ ነው፡፡
ከባለቤቱ በላይ የማንጨነቀው እኛ ባለቤት እንዳልሆንን እኛ አስተዳዳሪ እንደሆንን ስንረዳ ብቻ ነው፡፡ ለእኛ የሚያስበውን ሃሳብ ያውቃል ብለን የምናርፈው እኛ ጋር ያለው ነገር ሁሉ ባለቤት እንዳለው ባለቤቱን እግዚአብሄር እንደሆነ ስንረዳ ብቻ ነው፡፡
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ደጋግመጋቢ #ባለአደራ #ባለቤት #አስተዳዳሪ #ታማኝ #በትጋት #ኀዘንተኞች #ደስ #ድሆች #ባለጠጎች #የሌለን  #ሁሉየእኛነው #ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment