Popular Posts

Monday, August 27, 2018

በመታዘዝ የእግዚአብሄርን መልካምነት በአመፅ ደግሞ የሰይጣንን ክፋት እንመሰክራለን

ማንኛውም ሰው በህይወቱ ነገሮችን እየቀመሰና እየተለማመደ ነው፡፡ ሰው ሁሉ በህይወቱ ስለ አንድ ነገር ጥቅም ወይም ጉዳት እየተማረ ነው፡፡ ሰው በህይወቱ ልምዱ ስለአንድ ነገር ጥቅምና ጉዳት እያጠና ይመሰክራል፡፡ ሰው በህይወቱ ከሚያገኘው ልምድ አንፃር ለመልካምም ለክፋትም እውነተኛ ምስክር ሊሆን ይችላል፡፡
ለምሳሌ የእግዚአብሄር ያልሆነውን ነገር ሁሉ ንቆ እግዚአብሄርን የተከተለ ሰው የእግዚአብሄርን መልካምነት ይቀምሳል ያጣጥማል፡፡ ሁሉን ትቶ የእግዚአብሄርን ሃሳብ የተከተለ ሰው የእግዚአብሄርን መልካምነት በህይወቱ ይመሰክራል፡፡
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። 1 የጴጥሮስ መልእክት 2፡2-3
እንዲሁም ሰው ደግሞ የእግዚአብሄር ሃሳብ ሲተውና ምኞቱን ሲከተል እንዲሁ ካለ ምስክር አይቀርም፡፡ እግዚአብሄርን የተከተለ ሰው የእግዚአብሄርን መልካምነት እንደሚመሰክር ሁሉ በእግዚአብሄር ሃሳብ ላይ ያመፀ ሰው እንዲሁ ስለሰይጣን ክፋትና ጨካኝነት ከምስክርነት ጋር ይመለሳል፡፡
ህይወት የልምምድና ምስክርነት መድረክ ነው፡፡ ስለ አንድ ነገር መልካምነትም ይሁን ክፋት የማይመሰክር ሰው የለም፡፡  
አንዳንድ ሰው እግዚአብሄርን በመታዘዙ የሆነ የቀረበት ነገር ያለ ይመስለዋል፡፡ አንዳንዱ ሰው እግዚአብሄር በማገልገሉ የሆነ ነገር እንደጎደለበት ይሰማዋል፡፡ እንዳንዱ ሰው እግዚአብሄርን ባያገልግል ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ያስባል፡፡  
እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል? አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፤ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል። ትንቢተ ሚልክያስ 3፡14-15
እግዚአዘብሄርን በከፍታና በዝቅታ ሁሉ ማገልገል ታላቅ እድል መሆኑን ተምሮ እግዚአብሄርን በማገልግል የሚቀጥል ሰው የእግዚአብሄርን ክብር እያየ ይሄዳል፡፡ እግዚአብሄርን በማገልገልህ ተጠቀምክ እንጂ አልተጎዳህም ብሎ የሚመክረውን ሰው ያለሰማ ሰው እግዚአብሄርን ማገልገል ምን ያህል እድል እንደሆነ የሚረዳው በእግዚአብሄር ላይ አምፆ የሰይጣንን ጭካኔ ሲረዳ ብቻ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄር መሀሪ እንደሆነ ተምሮ በቅንነት ካልተቀበለ ሰይጣም ምን ያህል ምህረት የለሽ እንደሆነ የሚያየውና የእግዚአብሄርን ምህረት የሚያደንቀው በእግዚአብሄር ስራ ላይ አምፆ ሲያየው ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄርን በማገልገሉ እንደተጎዳ በቅንንነት የሚያምን ሰው እግዚአብሄር ምን ያህል መልካም እንደሆነ የሚማረው በእግዚአብሀር ላይ እምፆ የሰይጣንን ክፋት ሲረዳ ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሄርን እያገለገለ የውጭው ነገር የሚያምረው እና ሰይጣን ያን ያህል ክፉ እንዳልሆነ የሚያስብ ሰው አደገኛ ሰው ነው፡፡ የሰይጣንና የእግዚአብሄር ልዩነት የሰማይና የሲኦል ያህል እንደሆነ ያልተረዳ ሰው አደገኛ ሰው ነው፡፡ በአመፅ ቀጥሎ የሰይጣንን ክፋት  በውጤቱ የተረዳ ሰው ሲመልስ ለእግዚአብሄር የሚጠቅም የክብር እቃ ይሆናል፡፡
ለእግዚአብሄር በመገዛትና ሰይጣንን በመቃወም እኩል እናድጋለን፡፡
እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡7
የእግዚአብሄርን መልካምነት ከተደራን እንደምንጠቀመው ሁሉ የሰይንን ክፋት ካልተረዳን እንጎዳለን፡፡ የሰይጣንን ክፋት በተረዳን መጠን የእርሱ የሆነን ምንም ነገር በሃሳባችን ፣ በንግግራችንና በድርጊታችን እንዳይኖር እንጠየፈዋለን፡፡ ሰው ከሃጢያት ጋር የሚጫወተው የሰይጣንን ክፋት በሚገባ ስላልተረዳ ነው፡፡ ሰው በህይወቱ አመፃ ውስጥ የሚገባውና በተዘዋዋሪ አመፀኛውን ሰይጣንን የሚከተለው የሰይጣንን ሌብነት ፣ አራጅነትና አጥፊነት ስለማይረዳ ነው፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
ሰይጣን ምህረት አልባነት የተረዳ ሰው የሰይጣን የሆነ ማንኛውም ነገር በህይወቱ እንዲኖር አይፈልግም፡፡
ሰው በክርስትና ህይወቱ የሚያድገው በእግዚአብሄር መልካምነት እውቀትና በሰይጣን ክፋት እውቀት ሲያድግ ነው፡፡ በክርስትና እያደግን በሄድን ቁጥር እግዚአብሄር እጅግ መልካም እንደሆነ እየተረዳን እንመጣለን፡፡ በክርስትና እንዲሁ እያደግን ስንመጣ የሰይጣንን ክፋት ይበልጥ እየተረዳን እንመጣለን፡፡ በክርስትና እያደግንም ስንመጣ ለእግዚአብሄር ይበልጥ እንሰጣለን፡፡ በክርስትና እያደግን ስንመጣ ደግሞ በህይወታችን የእርሱ የሆነ ምንም አመፃ እና ሃጢያት እንዳይኖር እየወሰንን ያለውን ማንኛውንም የሰይጣን ነገር ከህይወታችን እያጸዳን እንመጣለን፡፡
አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። የይሁዳ መልእክት 123
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #መታዘዝ #አመፃ #ሰይጣን #ቤተክርስትያን #ሊሰርቅ #ሊያርድ #ሊያጠፋ #መስክርነት #መልካም #ክፋት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment