Popular Posts

Follow by Email

Monday, August 13, 2018

የስጦታዎች ሁሉ ስጦታ

ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ካለምክንያት እንዲሁ ስለወደደን ልጁን ኢየሱስን ላከልን፡፡ በበደላችንና በሃጢያታችን ሙታን በነበረን ጊዜ ስለሃጢያታችን እንዲሞት ልጁን ሰጠን ፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። የዮሐንስ ወንጌል 3፡16
እግዚአብሄር ልጁን ስለሃጢያታችን በመክፈል ልጆቹ አደረገን፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። 1 የዮሐንስ መልእክት 3፡1
አባት ለልጁ ይራራል፡፡ እግዚአብሄር ግን እኛን ያለምክንያት ስለወደደን ልጁን ሳይራራ ስለእኛ በመስቀል ላይ እንዲሰቀል ፈቀደ፡፡
እግዚአብሄር ለአንድ ልጁ ሳይራራለት ልጁን ስለሃጢያታችን ከሰጠን ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
እግዚአብሄር ሁሉን ይሰጠናል፡፡
ልጅን ከመስጠት አንፃር ሌሎች ስጦታዎች ሁሉ በጣም ቀላልና እዚህ ግቡ የማይባሉ ናቸው፡፡ ልጅን መስጠት የስጦታዎች ሁሉ ስጦታ ነው፡፡ ልጁን የሰጠን ጌታ ከሚያስፈልገን ነገር አንዳችንም የሚያጎድልብን ነገር አይኖርም፡፡
እግዚአብሄር እረኛችን ነው የሚያሳጣን የለም፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙረ ዳዊት 23፡1
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅ #እረኛ #ፍቅር #መስቀል #ስጦታ #መሪነት #ያበረታል #ያፅናናል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment