ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ወደ
ኤፌሶን ሰዎች 5፡23
ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን መሪ ነው፡፡ ክርስቶስ
የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፡፡ ማንም ሰው የቤተ ክርስቲያን ዋና የለም፡፡ ሁሉም ሰው በክርስቶስ ራስነት ጥላ ስር ነው፡፡ ክርስቶስ
በቤተ ክርስቲያን ዋና ነው፡፡ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ገዢ ነው፡፡
እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡18
ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ
እንደምትገዛ እንዲሁ
ሚስቶች ደግሞ
በሁሉ ለባሎቻቸው
ይገዙ። ወደ ኤፌሶን
ሰዎች 5፡24
ማንም ሰው ቤተ ክርስቲያንን አልመሰረተም፡፡ ቤተ
ክርስቲያንን የመሰረተው ኢየሱስ ነው፡፡
እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የማቴዎስ ወንጌል 16፡18
ቤተ
ክርስቲያን የማንም ግለሰብ አይደለችም፡፡ ሁላችን የዚህ የክርስቶስ አካል የቤተ ክርስቲያን ብልቶች ነን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ
አካል ነች፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ነች፡፡
እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤
እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡18
ክርስቶስ የቤተክርስትያነ አዳኝ ነው፡፡
ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡23
ቤተክርስትያን ክርስቶስ እንደወደደው የሚያሳምራትና
ለራሱ የሚያዘጋጃት የክርስቶስ ሙሽራ ነች፡፡
ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡25-27
ቤተክርስትያን
የመጋቢዎች አይደለችም፡፡ ቤተክርስትያን የሽማግሌዎች አይደለችም፡፡ የቤተክርስትያን መጋቢዎች ባለአደራ መጋቢዎች ናቸው፡፡
የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን
የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡4
የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች የመንጋው ባሌቤቶች
ሳይሆኑ ክርስቶስ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ይጠብቁ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ የተሾሙ ባለአደራዎች ናቸው፡፡
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን
ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። የሐዋርያት ሥራ 20፡28
ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በክርስቶስ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን የመጨረሻ ባለስልጣን ክርስቶስ ነው፡፡
ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም
ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስቲያን #ህብረት #አምድ
#መሰረት #ራስ #መሪ #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተ ክርስቲያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም
#አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment