Popular Posts

Tuesday, August 7, 2018

ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ

የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና። የያዕቆብ መልእክት 1፡9-10
በምድር ላይ የሚያስመካ ምንም ዘላቂ ነገር የለም፡፡ ከሰማይ በታች ሁሉ ጊዜያዊ ነው፡፡ ከምድር በታች ዘላቂ ነገር የለም፡፡ አበባ የመሰለ የሚያምር ነገር ይጠወልጋል፡፡ ባለጠጋ ይደክማል፡፡ መልክና ውበት ይጠፋል፡፡
ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል። የያዕቆብ መልእክት 111
የሚታየው ነገር ሁሉ የጊዜው ነው፡፡ የሚታየው ነገር ራሱም ስለሚለወጥ ሰውን ሊያስመካ አይችልም፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
 እነዚህ የት ይደርሳሉ የተባሉ ሃያል ሰዎች ይደክማሉ፡፡ ጎበዞች ጉልበት ይከዳቸዋል፡፡ የሰው ወጣትነትም ጉብዝናም አያስተማምንም፡፡
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡30
ሰውን የሚያስመካው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ካልተመካ በምንም መመካት አይችልም፡፡ ባለ ጠጋም በብልጥግናው ሳይሆን እግዚአብሄር ያበረታዋልና በውርደቱ ቢመካ ያምርበታል፡፡ ባለጠጋ በብልጥግናው ከሚመካ ይልቅ የተዋረደ ወንድም የተዋረደን በሚያከብር በእግዚአብሄር ቢመካ አስተማማኝ ተስፋ አለው፡፡  
የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና። ያዕቆብ 19-10
በሚያልፍ ነገር መመካት ኪሳራ ነው፡፡ በማያልፈው በማይደክመው ማስተዋሉ በማይመረመረው በእግዚአብሄር መመካት ብቻ አስተማማኝ መሰረት አለው፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።  ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡28-29፣31
የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና። የያዕቆብ መልእክት 19-10
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 923-24
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጥበብ #ማስተዋል #መረዳት #ሃያል #ጠቢብ #ባለጠጋ #ውርደቱ #ይመካ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment