Popular Posts

Follow by Email

Tuesday, August 21, 2018

ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ደም አፍስሰሃል፥ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 22፡8
እግዚአብሔር ግን፦ የሰልፍ ሰው ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም ብሎኛል። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፡3
በእግዚአብሄር ቤተክርስትያን እንዴት መኖር እንዳከለብን ማወቅ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ላለመጎዳት ሁሉን እርግፍ አድርጎ ይተወዋል፡፡ ሁሉን እርግፍ አድርጎ የሚተወው ሰው እግዚአብሄር ለቤተክስርትስቲያን ህብረት በውስጡ ያስቀመጠውን ስጦታ ይገለዋል፡፡ እግዚአብሄር ለሌሎች ጥቅም መነሳትና መበርታት በውስ ያስቀመጠውን ልዩ ለዩ ስጦታ ይቀብረዋል፡፡
አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡6-7
እንዲሁም እግዚአብሄር በህብረት ያስቀመጠውን በረከት ያመልጠዋል፡፡
ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና። መዝሙረ ዳዊት 133፡1፣3
ሌላው ደግሞ በህጉ ሳይጫወት ለአካሉ ብልቶች ሳይጠነቀቅ ሁሉንም ደርምሶ የራሱን ፍላጎት ብቻ ሊያሳካ ሲፈልግ የደም ሰው ይሆናል፡፡ በአላማ የማይታገል ሰው ሰውን ይጎዳል ፣ ቤተክርስቲያንን ይረብሻል ለብዙዎች መሰናከል ምክንያት ይሆናል የብዙዎችን ልብ ያሳዝናል፡፡
በእግዚአብሄር ቤተክርስትያን እንዴት መኖር እንዳለብን መማር ያለብን ላለመጎዳት ከቤተክርስቲያን ፈፅሞ ከመሸሽና ለከሌላው ሳይጠነቀቁ ብዙዎችን ለራስ ጥቅም ከማሳዘንና የደም ደስ ከመሆን ለመጠንቀቅ ነው፡፡  
ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡15
እግዚአብሄርን ለማገልገል ራእይ ያለው ሰው ከእነዚህ ነገሮች ራሱ ያነፃል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ እንዳያዝንበት የሚጠነቀቅ ሰው ከውሸት ፣ ከምሬት ፣ ከጥል ፣ ከስድብ እና ከክርክር ይርቃል፡፡
ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡25-30
እግዚአብሄር በሃይል እንዲጠቀምበት ተስፋ የሚያደርግ ለሚያልፍ ቀን ራሱን በእነዚህ ነገሮች አያቆሽሽም፡፡ የእግዚአብሄን ስራ ለመስራት ተስፋ ያለው ሰው ከእነዚህ ነገሮች ራሱን ያነፃል፡፡ ለጌታ የሚጠቅም እቃ መሆን የሚፈልግ ሰው የከበረውን ከተዋረደው ይለያል፡፡  
በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል።  2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡20-21
በህይወቱና በአገልግሎቱ የእግዚአብሄርን መንፈስ መገኘት እንዳያጣው የሚፈልግ ሰው በውዝግብ መካከል ለአስተሳሰቡ ለአንደበቱና ለድርጊቱ ይጠነቀቃል፡፡ እግዚአብሄርን በስፋት ለማገልገል ራእይን ያረገዘ ሰው ከውሸት ፣ ከአድመኝነት ፣ ከሃሜት ፣ ከጥልና ከክርክር ይሸሻል፡፡
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ደም አፍስሰሃል፥ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 22፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ቅዱስ #ክፉ #ውሸት #ሃሜት #ጥልና #ክርክር  #ቁጣ #አድመኝነት #ምሬት #ቅድስና #እርኩሰት #የተቀደሰ  #ለክብር #ለውርደት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ተስፋ #ያነፃል #ክብር #ውርደት

No comments:

Post a Comment