በእናንተ
ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ። ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡24
የምንኖረው
ለራሳችን አይደለም፡፡ የምንኖረው ለጌታ ነው፡፡
ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤ ወደ ሮሜ ሰዎች
14፡7
እኛ በሃጢያታችን ምክንያት ሟች ነበርን፡፡ አሁን የምንኖረው ስለእኛ ለሞተልን ለጌታ
የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ
ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡15
በክርስቶስ ስም ተጠርተናል፡፡ የክርስቶስንም ስም ተሸክመን እንኖራለን፡፡
ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ
ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ የሐዋርያት ሥራ 9፡15
የምናደርገው ነገር ሁሉ ክርስቶስን ያከብራል ወይ ክርስቶስን ያሰድበዋል፡፡ የእግዚአብሄርን
ቃል ስንኖርና መልካም ነገር ስናደርግ ሰዎች የተሸከምነውን የክርስቶስን ስም ነው እንጂ እኛን አያዩም፡፡ ክፉም ነገር ስናደርግ
የተሸከምነውን የኢየሱስን ስም እንጂ እኛን አያዩም፡፡
መልካሙን
ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡16
የእግዚአብሄርን
መንግስት ስም እንደተሸከመ ሰው በሃላፊነት እንኑር፡፡ የእግዚአብሄርን ልጅ የክርስቶስን ስም እንደተሸከመ ሰው በጥንቃቄ አንመላለስ፡፡
የእግዚአብሄርን ስም እንደተሸከመ ለመንግስቱ ሃላፊነት እንደሚሰማው ሰው እናስብ እንናገር እናድርግ፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት
#ወንጌል #ስብከት #ቃል #ስም #ይመሰገናል #ይሰደባል #ይከብራል #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment