እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው
የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ዘፍጥረት 1፡26-27
ሰው
በሃጢያት ምክኒያት ያጣው በጣም ወሳኝና አስፈላጊ ነገር የእግዚአብሄርን መልክና ክብር ነው፡፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23
ኢየሱስ
ወደ ምድር የመጣው በሃጢያት ምክኒያት የጠፋውን የእግዚአብሄርን መልክ ለመመለስ ነው፡፡
ኢየሱስን
የተቀበልን ሁላችን ከሁሉም ነገር በላይ አላማችን እና ግባችን እግዚአብሄርን መምሰል መሆን አለበት፡፡
የእግዚአብሄር
ፀጋ ለሁላችን የተዘጋጀው እግዚአብሄርን እንድንመስል ነው፡፡
ሰዎችን
ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም
የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም
በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፡11-13
እግዚአብሄርን
እንድንመስል የሚያስፈልገን ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡
የመለኮቱ
ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና
በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3
የማንኛውም
አገልጋይ ተልእኮ ሰዎች እግዚአብሄርን እንዲመስሉ ማስተማርና መርዳት ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ የተላከው ሰዎችን እግዚአብሄርን ወደ
መምሰል እንዲመራ መሆኑን ስለአገልግሎቱ ይመሰክራል፡፡
የእግዚአብሔር
ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ
አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ቲቶ 1፡1
መፅሃፍ
ቅዱስ የሚያስጠነቅቀው የአምልኮ መልክ ያላቸውን ሃይሉን ግን የካዱትን ነው፡፡
የአምልኮት
መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡5
እግዚአብሄርን
መስለው የሚኖሩ ሰዎች እንደሚሰደዱ መኝሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ እግዚአብሄርን መሰለው ለሚኖሩ ሰዎች ነገሮች ቀላል አይሆኑም፡፡
በእውነትም
በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡12
እግዚአብሄርን
መምሰል ነገሮችን የማግኛ መንገድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን መምሰል የመጠቀሚያ መንገድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን መምሰል በራሱ
ግብ ነው፡፡ እግዚአብሄርን መምሰል ወደ ጥቅም መሸጋገሪያ መንገድ ሳይሆን ራሱ ጥቅም ነው፡፡ እግዚአብሄርን መምሰል ወደ እድል መተላለፊያ
መንገድ ሳይሆን ራሱ እድል ነው፡፡
ኑሮዬ
ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር
#ጌታ #መከተል #መከተል #መምሰል #እግዚአብሔርንመምሰል #ቃል #ተማሪ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #ተከታይ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment