Popular Posts

Saturday, July 14, 2018

አምነናል ጉልበት አለህ - ክፋት ማድረግ ትችላለህ

ብዙ ሰዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ክፋትን ያደርጋሉ፡፡ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ክፋትን የሚያደርጉት ለራሳቸው ለመጠቀም ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች ክፋትን የሚያድርጕት ለመጠቀም ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ክፋትን የሚያደርጉት ለመጉዳት ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ክፋትን የሚያደርጉት ጉልበታቸውን ለማሳየት ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ክፋትን የሚያደርጉት እኔነታቸውን ለማርካት ብቻ ነው፡፡  
ሰዎች ክፋትን የሚያደርጉት በቅናት ተነሳስተው ነው፡፡ ሰዎች ክፋትን የሚያደርጉት ጉልበታቸውን ለማሳየት ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ጉልበት እንዳላቸው እንኳን እርግጠኛ አይደሉም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ካላቸው የበታችንት ስሜት የተነሳ ክፋትን በማድረግ የበላይነት ስሜት ያሳያሉ፡፡
የበላይነት ስሜት የሚመጣው ከበታችነት ስሜት ነው፡፡ የበታችነት ስሜት የሚሰማውና በራሱ መተማመን የሌለው ሰው ሰዎች አይቀበሉኝም አያምኑብኝም ጉልበት የለውም ብለው ያስባሉ ብሎ ስለሚያስብ ጉልበት እንዳለው ለማሳየት በበላይነት ስሜት ይገለጣል፡፡ የበታችነት ስሜት የሚይሰማው ሰው የበላይነት ስሜት እንዲያሳይ አያስፈልገውም፡፡ ሰው የበላይነት ስሜት የሚያሳየው የበታችነት ስሜት ሲሰማው ነው፡፡
የበላይነት ስሜት ያለው ሰው ብታዩ ከጀርባው የበታችነት ስሜት አለ፡፡ የበታችነት ስሜት ያለበት ሰው ደግሞ የበታችንት ስሜቱን የሚያካክስው ረብሻ በመፍጠር በመጣላትና በመረበሽ በዚያም የበላይነቱን በማሳየት ነው፡፡
ሰው በእግዚአብሄር አምሳል ተፈጥሮአል፡፡ ሰው በውስጡ ትልቅ እምቅ ጉልበት አለው፡፡ ሰው መልካምም ይሁን ክፉ ለማድረግ ትልቅ እምቅ ጉልበት አለው፡፡ ሰው ደግሞ ያለውን ሃይል ለክፋትም ይሁን ለመልካምነት ለመጠቀም ነፃ ፈቃድና ምርጫ አለው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ክፉ አታድርጉ የሚለው እኮ ክፉ ማድረግ እንደምንችል ስለሚያውቅ ነው፡፡
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡29
መፅሃፍ ቅዱስ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ቃል ብቻ ተናገሩ ሲል በተቃራኒው የሚሰሙትን የሚያፈርስ የሚጎዳ ቃል ማውጣትና ማፍረስ ትችላላችሁ እያለን ነው፡፡ ስለዚህ ማፍረስ እንደምንችል ጥያቄ የለውም፡፡  
የሚገነባ የሚጠቅምና የሚያንፅ ቃል በውስጣችን እንዳለ ሁሉ የሚያፈርስ የሚበትንና የሚጎዳ ቃል በውስጣችን አለ፡፡  
ስለ እነዚህ ነገሮች ማሳሰብህን አትተው፤ በቃላት እንዳይነታረኩ በእግዚአብሔር ፊት አስጠንቅቃቸው፤ ይህ ጥቅም የሌለው፣ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡14
አዎ እኛም አምነናል ማፍረስ ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ማፍርስ ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ማፍረስ እችላለሁ በል ነገር ግን ላለማፍርስ ሃላፊነትን ወሰድ፡፡ ማፍረስ እንደምትችል አትጠራጠር፡፡ ማፍረስ እንደምትችል እወቅ ነገር ግን ያለህን ጉልበት ለመገንባት እንጂ ለማፍረስ ላላመጠቀም ወስን፡፡ ማፍረስ ብርቅ አይደለም፡፡ ማፍረስ ከባድም አይደለም፡፡ ላንተ ግን አይጠቅምህም፡፡ አንተን ግን ይጎዳሃል፡፡ የምታፈርሳቸውን ሰዎች ይጎዳል፡፡
የዋህ ማለት ደካማ ሃይል የሌለው ሰው ማለት አይደለም፡፡ የዋህ ማለት ለማፍርስ ፣ ለማበላሸትና ለመበተን ሃይል ሁሉ ኖሮት ሃይሌን ለመልካምነት እንጂ ለክፋት አልጠቀምም ብሎ ራሱን የሚገዛ ነው፡፡ የዋህ ሃይል የለም ብሎ አምኖ ክፋትን ከማድረግ የሚመለስ ሰው አይደለም፡፡
የዋህ ሃይሌን ለክፋት መጠቀም አይመጥነኝም አይገባኝም የሚል ሰው ነው፡፡ የዋህ ሃይሉን ለክፋት ለመጠቀም ህፃን ያልሆነ ሰው ነው፡፡ የዋህ ሃይሉን ለክፋት ላለመጠቀም የበሰለ ሰው ነው፡፡  
ቀናተኛ የሆነ ሰው ግን ሃይሉን ለማሳየት አይመርጥም ክፋትንም ቢሆን ይጠቀማል፡፡ ሃይሉን ያሳይለት እንጂ ሃይሉን ለጥፋት ፣ ለመበተንና ለማፍረስ ለመጠቀም አይፈራም፡፡ ቀናተኛ ሰው እኔነቱን ለማርካት ሰዎችን ሲያፈርስ ሲበትን ሲያቆስል አይፈራም፡፡
ቀናተኛ ሰው ህፃን ስለሆነና ሃይል እንዳለው እንኳን እርግጠኛ ስላይደለ ሃይሉን የሚሞክረው በማፍርስ ፣ በመበተንና በማቁሰል ላይ ነው፡፡ ቀናተኛ ሰው ሃይሉን የሚሞከርው በክፋት ላይ ነው፡፡
ሰው ሆይ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ሃይልህን ለክፋት አትጠቀም፡፡ ክፋት ማድረግ እንደምትችል አታሳየን ቀድመን እናውቃለን፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #የዋህ #ክፋት #ልብ #መንፈስ #ማነፅ #መጥቀም #ማፍረስ #ክፉ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment