አንድ ጊዜ የከበባቸውን የጠላትን ሰራዊት ብዛት ተመልክቶ የነብዩ የኤልሳ ሎሌ ልቡ ተሸበረ፡፡
የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡15
የኤልሳ ሎሌ ችግሩ የእግዚአብሄር እርዳታ ከእርሱ ጋር አለመሆኑ ሳይሆን የእግዚአብሄርን እርዳታ ማየት አለመቻሉ ነው፡፡ የኤልሳ ሎሌ ሰለከበቡዋቸው የጠላት ሰራዊት ብዛት ሲሸበር አይቶ እግዚአብሄር የብላቴናውን አይን እንዲከፍት ፀለየ፡፡
ኤልሳዕም፦ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡17
እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡16
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ የልቦናችን አይኖች እንዲበሩ መፀለይ እነዳለብን የሚያስትምረው፡፡ የጎደለን ሃይል አይደለም የእግዚአብሄር ሃይል ከእኛ ጋር ነው፡፡ የጎደለን እርዳታ አይደለም የእግዚአብሄር መንግስት እርዳታ ከእኛ ጋር ነው፡፡
የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡17-19
በእኛ ውስጥ ያለው በአለም ካለው ይልቅ ታላቅ ነውና፡፡
ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡4
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ራዕይ #ምሪት #ድል #የእግዚአብሄርፈቃድ #የእግዚአብሄርአላማ #የእግዚአብሄርምክር #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተግዳሮት #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አይን #እይታ #አጥርቶ #ራእይ #መሪ
No comments:
Post a Comment