Popular Posts

Wednesday, July 25, 2018

የመሪነት ችግር የእግዚአብሄር ችግር ነው

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረበት ምክንያት እግዚአብሄር ሰውን በሚገባ እንዲመራውና ሰው እግዚአብሄርን በሚገባ እንዲከተለው ነው፡፡
ሰው እግዚአብሄርን በተከተለ ጊዜ ሁሉ በስኬትና በብልፅግና ይኖር ነበር፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በተከተለበት ጊዜ ሁሉ ምንም አይነት የመሪነት ችግሮች በምድር ላይ አልነበረም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በተከተለበት ጊዜ ሁሉ በሰው ስር ያሉ ተከታዮች ሁሉ ሰውን በሚገባ ይከተሉት ነበር፡፡
ሰው እግዚአብሄርን መከተል ሲያቆም ከስሩ ያሉ የሚመራቸው ነገሮች ሁሉ እርሱን መከተል አቆሙ፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በተከተለበት ጊዜ ሁሉ ምድር የሃይሏን መጠን ሁሉ ትሰጠው ነገር፡፡ ሰው እግዚአብሄር ላይ ባመፀና እግዚአብሄርን መከተል ባቆመ ጊዜ ምድር ሰውን መከተሏንና የሃይሏን መጠን መስጠት አቆመች፡፡
እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ ኦሪት ዘፍጥረት 3፡18-19
ሰው መሪነትን የሚማረውና የሚለማመደው ከእግዚአብሄር ጋረ ባለው መሪነትና ተከታይነት ሂደት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲከተል ሰው እንዴት ባለስልጣንን እንሚከተል ይማራል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲከተል ሰው ሰውን እንዴት እንደሚመራ ከእግዚአብሄር መሪነት ምሳሌን ያገኛል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄርን ከሰው መሪነትና ተከታይነት ለራሱ መሪነት ስልጣን ያገኛል፡፡ የሰው እግዚአብሄርን መከተል የመሪነት ትምህርት ቤት ነው፡፡ የሰው እግዚአብሄር እንዴት እንደሚመራ ማየትና እግዚአብሄርን መከተል የተከታይነት ትምህርት ስልጠና ነው፡፡
ሰው እግዚአብሄርን መከተል ሲያቆም የመሪነትን ትምህርት አጣው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን መከተል ሲያቆም እንዴት እንደሚመራ ስልጣኑ ጠፋበት፡፡ ሰው እግዚአብሄርን መከተል ሲያቆም ሌላውን እንዴት እንደሚከተል ምሳሌውን አጣው፡፡
የሰው እግዚአብሄርን መከተል ችግር የመሪነትና የተከታይነት ችግር ሁሉ መንስኤ ነው፡፡ የሰው እግዚአብሄርን መከተል የሰው የመሪነትና የተከታይነት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ነው፡፡
እግዚአብሄርን እንዴት በትህትና እንደሚከተል የሚያውቅ ሰው ሌሎችን ባለስልጣኖች እንዴት እንደሚከተል ይማራል ያውቃል፡፡ የሰው የመከተል ችግር የመነጨው ከሰው እግዚአብሄርን ከመከተል ችግር ነው፡፡ የሰው ሰውን የመከተል ችግር የሚመነጨው እግዚአብሄርን ከመከተል ችግር ነው፡፡ የሰው እግዚአብሄር በህይወቱ ላይ ያስቀመጠውን ስልጣን የመከተል ችግር ወደኋላ ቢጠና የሰው እግዚአብሄርን የመከተል ችግር ላይ ይደረሳል፡፡ የሰው ለስልጣን ያለመገዛት ችግር መሰረቱ የሰው ለእግዚአብሄር ያለመገዛት ችግር ነው፡፡
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8
ሰው በትህትና እንዴት ለእግዚአብሄር እንደሚገዛ ካወቀ ለሰው ስልጣን እንዴት እንደሚገዛ ያውቃል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር እንዴት እንደሚገዛ ካላወቀ ለሰው ይገዛል ብሎ መጠበቅ ሞኝነይ ነው፡፡ የሰው ለምድራዉ ባለስልጣን መገዛት የሚያመለክተው ሰው ለእግዚአብሄር ቃል ስልጣን መገዛትን ነው፡፡
ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1-2
የሰው ለስልጣን ያለመገዛት ችግር የሚፈታው ሰው ለእግዚአብሄር ቃል ትሁት ሲሆን ለእግዚአብሄር መገዛትን ሲማር ብቻ ነው፡፡ የሰው የመሪነት ችግር የሚፈታው የሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የመሪና ተከታይነት ግንኙነት ሲስተካከል ነው፡፡ የሰው የተከታይነት ችግር የሚፈታው ለእግዚአብሄር መሪነት ያለው ተከታይነት ሲስተካል ነው፡፡ የሰው ሌሎችን የመምራት ግንኙነት የሚስተካከለው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የመሪነት ግንኙነት ሲስተካከል ብቻ ነው፡፡ የሰው የመሪነት ስልጣን የሚገኘው ለእግዚአብሄር ካለው የተከታይነት ስልጣን ነው፡፡
እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 8፡9
የሰው የመታዘዝ እና ለስልጣን የመገዛት ችግር የእግዚአብሄር ችግር ነው፡፡ የሰው ከስልጣን ጋር ያለው ግንኙነት ችግር የሚመነጨው ከእግዚአብሄ ጋር ካለው የስልጣነ ግንኙነት ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር መገዛትን በተማረ ቁጥር ለስልጣን መገዛትን ይማራል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር በተገዛ ቁጥር ሌሎች ለስልጣኑ እንዲገዙ ስልጣኑ ይጨምራል፡፡ ለእግዚአብሄር ስትገዛ ሁሉም ነገሮች ለእግዚአብሄር እንደሚገዙ ይገዙልሃል፡፡
ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። መጽሐፈ ምሳሌ 3፡1፣4
ሰው በእግዚአብሄር ፊት ያለው ሞገስ ሲጨምር በሰው ዘንድ ያለው ሞገስ ይጨምራል፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ ያንን ሁሉ ስልጣን ያገኘውና የተለማመደው ከእግዚአብሄር ጋር ባለው የተከታይነት ሞገስ መጨመር ነው፡፡
ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 2፡52
ሰው በምድር ያለውን ስልጣን ለመጨመር ከሰው ጋር ከመጣላት ከእግዚአብሄር ጋር መስማማት የሚፈልገውን ስልጣን እንዲለማመድ ያስችለዋል፡፡
አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። መጽሐፈ ኢዮብ 22፡21
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሃይል #ስልጣን #መገዛት #መከተል #መሪነት #ጥበብ #ክፉ #መልካም #ፍርድ #እውቅና #ፍፁም #ችግር #መፍትሄ #አላማ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment