የሰራዊት
ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ለእናንተ የማስባትን አሳብ
እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11
እግዚአብሄር
የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረውን ነገር ሁሉ የፈጠረው በአላማ ነው፡፡ ሰው በድንገት የተገኘ ፍጥረት አይደለም፡፡
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር አላማ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለተለየ አላማ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት
አስቦበትና አቅዶ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት እንደሰው አይነት ፍጥረትን እንደሚፈጥር በአይነ ህሊናው ስሎ አስቦበት
ነው፡፡
እግዚአብሄር
ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ሰው ምን እንዲያደርግለት እንደሚፈልግ ወስኖ ነበር፡፡ ሰው ከመፈጠሩ በፊት ህይወቱ ከምን ጀምሮ በምን እንደሚፈፅም
በእግዚአብሄር ተወስኖ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት እንደሰው ያለ ፍጥረትን በምድር ላይ እንዲኖር ፈልጎ ነበር፡፡
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በምድር ላይ እንዲኖር የሚፈልገውን አይነት ፍጥረት አድርጎ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው አቅዶና
አልሞ የፈጠረው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ልብ ውስጥ የተወሰነውን አላማ ለማስፈፀም ነው፡፡
እያንዳንዳችን
ወደምድር ከመፈጠራችን በፊት በምድር ላይ እንድንሰራው የተወሰነ ነገር ነበር፡፡ በምድር ላይ መፈጠራችን የሚያመለክተው እግዚአብሄር
አስቀድሞ እንድንፈፅመው ያዘጋጀው ስራ እንደነበረ ነው፡፡
እኛ
ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ወደ
ኤፌሶን ሰዎች 2፡10
ማናችንም
የራሳችን አይደለንም፡፡ እኛ የእግዚአብሄር ነን፡፡ ማንም ሰው ለራሱ የህይወት እቅድ መስጠት የለበትም፡፡ ሰው ለራሱ የህይወት እቅድ
መስጠት አይችልም፡፡
እግዚአብሄር
ለእኛ ህይወት አቅድ አለው፡፡ ወደእግዚአብሄር የምንፀልየው የህይወት እቅድ ሃሳብ ልንሰጠው ሳይሆን የህይወት እቅዳችንን ከእርሱ
ለመቀበልና በህይወት እቅዳችን ላይ በትጋት ከሚሰራው ከእግዚአብሄር ጋር አብረን ሰራተኛ ለመሆን ነው፡፡
ለእናንተ
የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥
ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11-12
እግዚአብሄር
የህይወት እቅዳችንን ከእናታችን ማኅፀን ጀምሮ የህይወት እቅዳችን እየሰራው ነው፡፡ እግዚአብሄር በህይወት ንድፋችን መሰረት እየመራን
ነው፡፡
በሆድ
ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 1፡5
ስለዚህ
ነው የህይወት እቅዳችን ለመንደፍ መጨነቅ የሌለብን፡፡ የህይወት እቅዳችንን መንደፍ አንችልም፡፡ የህይወት እቅዳችን ተነድፎ ያለቀ
ነው፡፡ ወደምድር የመጣንበት ምክንያት የህይወት እቅዳችንን ለመከተልና ለመፈፀም ነው፡፡ በህይወት ማድረግ የምንችለው አንድ ነገር
የህይወት እቅዳችንን ከእግዚአብሄር ተቀብለን እግዚአብሄር የህይወት እቅዳችንን ሲሰራው አብረን መተባበር ብቻ ነው፡፡
ኢየሱስ
ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 5፡17
እኛ
የህይወታችን ባለ አደራ እንጂ ባለቤት አይደለንም፡፡ ህይወታችን ባለቤት አለው፡፡ የህይወታችን ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡ የህይወታችን
እቅድ ያለው አግዚአብሄር ጋር ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደባለቤት በህይወት አቅዳችን ላይ በትጋት እየሰራበት ነው፡፡ እግዚአብሄር
እኛን የሚፈልግን እቅድ እንድናወጣ ሳይሆን እግዚአብሄር በትጋት እየሰራበት ባለው የህይወት እቅዳችን ላይ ተባብረን አብረነው እንድንሰራ
ነው፡፡
ስለዚህ
ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤
ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። የዮሐንስ ወንጌል 5፡19
በህይወታችን
የራሳችንን እቅድ ማቀድ የለብንም፡፡ በህይወት ውጤታማ የምንሆነው በህይወት እቅዳችን ላይ በትጋት ከሚሰራው እግዚአብሄርን ጋር በመተባበር
ብቻ ነው፡፡
ለእናንተ
የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ
29፡11
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተስፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment