Popular Posts

Saturday, July 7, 2018

በህይወት ለማረፍ ብቸኛው መንገድ

በህይወት ለማረፍ የማይፈልግ ሰው የለም፡፡ ሁላችንም ለማረፍ እንፈልጋለን፡፡ እረፍት ይጣፍጣል፡፡
ጥያቄው ግን እንዴት ማረፍ እንችላለን ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች በምድር ላይ ማረፍ አይቻልም ብለው ተስፋ ቆርጠው ነገር አለሙን ትተውታል፡፡ ነገር ግን በሰማይ ብቻ ሳይሆን አሁን በምድር ላይም ቢሆን ማረፍ ይቻላል፡፡
በአለም ያለውን ተግዳዳሮት ሁሉ ሲያዩ በዚህ አለምማ እረፍት የሚታሰብ አይደለም ብለው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
አንዳንዶች ደግሞ ማረፊያ ሌላ መንገድ ለራሳቸው ያዘጋጃሉ፡፡ እረፍትን ለማግኘት የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋሉ፡፡ እረፍት የሆነ ነገር በማድረግ ውስጥ አይመጣም፡፡ ሰዎች እረፍትን ለማግኘት የተለያዩ ነገሮችን እንዲኖራቸው ይፈደልጋሉ፡፡ እረፍት ገንዘብና ቁሳቁስን በማከማቸት አይመጣም፡፡ ሰዎች እረፍትን ለማግኘት የተለያየ ነገርን ይሆናሉ፡፡ እረፍት ስመጥር እና ዝነኛና በመሆንም አይመጣም፡፡
እውነተኛ እርፍት የሚመጣው በራሳችን ባዘጋጀነው መንገድ ሳይሆን እግዚአብሄር ባዘጋጀው መንገድ ብቻ ነው፡፡
ታዲያ ከእግዚአብሄር የሆነው እውነተኛው እረፍት ማረፍ የሚመጣው በእምነት ነው፡፡
በአለም ያለው ተግዳሮት እያለ በእረፍት ማረፍ ይቻላል፡፡ በአለም ያለው ጨለማ እያለ በብርሃነ ማረፍ ይቻላል፡፡ በአለም ያለው ጦርነት ሁሉ እያለ ሰው በእግዚአብሔር ሰላም ሊያርፍ ይችላል፡፡
ሰው እንዲያርፍ በአለም ላይ በየጊዜው የሚነሳው ተግዳሮት መቆም የለበትን፡፡ ሰው በተግዳሮት መካከል ሊያርፍ ይችላል፡፡ ሰው እንዲያርፍ ገንዘቦች ሁሉ ወደኪሱ መግባት የለባቸውም፡፡ ገንዘቦች ባይመጡም ሰው በእግዚአብሄር ማረፍ ይችላል፡፡ ሰው እንዲያርፍ ጦርነት መቆም የለበትም፡፡ በጦርነት መካከል ሰው ሰላም ሊኖረው ሊያርፍና ህይወቱን ሊደሰትበት ይችላል፡፡
ህይወትን እንደሸክም ብቻ ሳይሆን እንደ ስጦታ ልንደሰትበት የምንችለው በእረፍት ነው፡፡  
እግዚአብሄር የሚኖረው በእረፍት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው የሚያስፈልገውን ሁሉ ከፈጠረና በኋላና ወደ እረፍት ሊገባ ሲል ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለእረፍት ነው፡፡
ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄርን በማየትና በመከተል ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄር በመስማትና በመከተል ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው ከአለም ድምፆች ሁሉ ውስጥ እግዚአብሄርን በመስማት ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡
ሰው የሚያርፍው እግዚአብሄር እንደሚያይ በማየትና እግዚአብሄር የሚያየውን በማየት ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው በእምነት ነው፡፡
እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ተስፋ ገና ቀርቶልን ከሆነ፥ ምናልባት ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንፍራ። ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። ወደ ዕብራውያን 4፡2-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #እረፍት #መደገፍ #ሰንበት #መታዘዝ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment