Popular Posts

Follow by Email

Thursday, July 5, 2018

የህፃንነት ልዩ ምልክቶች

ብዙ ጊዜ የምናተኩረው በክርስቶስ ስለተደረገልን ነገር ነው፡፡ በክርስቶስ የተደረገልን ነገር ሁሉ ያልለፋንበት ስጦታ ነው፡፡ በክርስቶስ ይህ ሁሉ ነገር ተፈደርጎልንም ለሃላፊነት የማንበቃ ህፃናት ልንሆን እንችላለን፡፡
ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡1-2
እግዚአብሄር ለብዙ ነገሮች ያምነን ዘንድ ከህጻንነት መውጣት አለብን፡፡
የህፃንነት ምልክቶች
1.      ትግስት ማጣት
ህጻን የሚያውቅው አሁንን ነው፡፡ ህጻን እቅድን አያውቅም፡፡ ህፃን ተስፋን አይረዳም፡፡ ህፃን የወደፊቱን ብዙም አያየም፡፡ ህጻን የሚያየውና የሚያውቀው አሁንን ነው፡፡ እንዲሁ በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው የቅርቡን ብቻ ያያል የሩቁን ማይት ተስኖታል፡፡
እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡9
በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው ወደፊቱን አያየም፡፡ በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው አሁን የሚያደርገው ነገር ነገር ስለሚያስከትልበት ችግር አይረዳም፡፡ በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰወ ስለሚዘራው ክፉ ዘአዘር አይጠነቀቅም፡፡
አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7-8
በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው መታገሉን እንጂ በሚገባ በህጉ መሰረት መታገሉን አያረጋግጥም፡፡
የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡4-5
2.     ሁሉንም ለመስራት መሞከር
ህፃን ለራሱ ያው አመለካከት የተዛባ ነው፡፡ ህፃን የማይችለውን የሚችለው ይመስለዋል፡፡ ህፃን በቀላሉ ይታለላል፡፡ ህጻን እርሱ ብቻ የሚችል ይመስለዋል፡፡ ህፃን ውስን እንደሆነ አይረዳም፡፡ ህፃን ሌላው የአካል ብልት የሚያደርገውን አይረዳም፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡20
3.     ራስን ከሌላ ጋር ማስተያየት
ህፃን የሆነ ሰው በመወዳር በቅናትና በፉክክር ህይወቱን ለማባከን አይፈራም፡፡
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡12
4.     ጥልና ክርክር
እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤
ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡1-3
5.     ክፍፍል እና አድመኝነት 
በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው ጥበብ ሁሉ አንድ አይነት ይመስለዋል፡፡ በክርስቶስ ያልበሰለ ሰው በምድርና በሰማይ ጥበብ መካከል ያለውን ልዩነት አያውቅም፡፡
ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። የያዕቆብ መልእክት 3፡13-17
6.     ተምሮ ወደ እውቀት አለመድረስ
ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።2 ወደ ጢሞቴዎስ 36-7
7.     የመንፈሳዊ መረዳት ጉድለት
መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡13
ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። ወደ ዕብራውያን 5፡12-14
8.     በፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት አለመረዳት
ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መክብብ 10፡16-17
9.     ቶሎ ሆድ ይብሰዋል
ህጻን ቶሎ ሆድ ይብሰዋል፡፡ ህጻን በአንድ ቦታ አይጸናም፡፡ ህጻን መከራን ከመታገስ ይልቅ መሸሽን ይመርጣል፡፡ ህፃን ወረተኛ ነው፡፡ በክርስቶስ ህፃንም የሆነ እንዲሁ ያገኘውን ነገር ወዲያው ያጋንነዋል ወዲያውም ያጣጥለዋል፡፡ ህፃን ጠንካራን ነገር ዋጥ አድርጎ የማለፍ ጉልበት የለውም፡፡
በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 24፡10
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #መሰረታዊፍላጎት #ቅንጦት #ማማጠን #ህፃን #ንጉስ #መኳንንት #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment