በዚች
ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። 1 ቆሮንጦስ 15፡19
እኛ
በአለም እንኖራለን እንጂ ከአለም አይደለንም፡፡ እኛ ከአለም አይደለንም፡፡
እኔ
ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም። የዮሐንስ ወንጌል 17፡16
ይህ
ምድር ጊዜያዊ መኖሪያችን ነው፡፡
እግዚአብሄር
ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ ሰው በምድር በምድር የተቀመጠው እንዲያስተዳድርና እንዲገዛ ብቻ እንጂ ሰው ከምድር ስለሆነ
አይደለም፡፡ ሰው የወጣው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ከምድር አይደለም፡፡
በምድር
ያለነው ወደ አለም ተልከን ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው የስራ ድርሻና ተልእኮ ስለለን ነው፡፡
ወደ
ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 17፡18
በምድር
የሚያቆየን የተላክንበት አላማ እንጂ ሌላ አላማ አይደለም፡፡ ዓለም የተገባችን አይደለችም፡፡
ዓለም
አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። ወደ ዕብራውያን 11፡38
ክርስቶስን
ተስፋ ያደረግነው ለዘላለም ህይወት ነው፡፡ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለእግዚአብሄር ልጅነት ህይወት ነው፡፡ ክርስቶስን ተስፋ
ያደረግነው ለአጭር የምድር ኑሮ ብቻ አይደለም፡፡ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው በምድር ለመኖር ከሆነ ከሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡
በክርስቶስ ያመንነው በምድር ደልቶን ለመኖር ከሆነ ከሁሉ በላይ የሚታዘንልን ምስኪኖች ነን፡፡
ክርስቶስን
የተከተልነው ትልቅ ቤት ውስጥ ለመኖርና የተሻለ መኪና ለመንዳት ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡
ክርስቶስን
የተከተልነው ዝነኛ ለመሆን ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡
የእምነት
አባቶች በምድሪቱ እንግዶችና መጻተኞች ክፉ ውድድር ውስጥ ሳይገቡ በእምነት ኖሩ፡፡
እነዚህ
ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች
እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ወደ ዕብራውያን 11፡13-14
የእምነት
አባቶች በምድሪቱ እንግዶችና መጻተኞች ሆነው ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሳቸውን ሳያጠላልፉ በእምነት ኖሩ፡፡
የሚዘምተው
ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡4
ምክኒያቱም
የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቁ ነበርና፡፡
አሁን
ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡16
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy
Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ክብር #ትዳር #ንግድ #ወታደር #ዘማች #መዋረድ #መከራ #ፈተና #መፅናት #መታገስ #እንግዶች #መጻተኞች #ምስኪኖች #ተስፋ #አለም #የተገባ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment