Popular Posts

Follow by Email

Friday, July 14, 2017

በምድር ያለንበት ዋናው ምክኒያት

የተፈጠርነውና በምድር ያለነው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ በምድር ያለነው ያለንበት ዋነኛው ምክኒያት ለመብላት ለመጠጣትና ለመልበስ አይደለም፡፡ በምድር ያለነው የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት ነው፡፡ በምድር ያለነው ስለእግዚአብሄ መልካምነርት ለመምሰከር ነው፡፡
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9
በምድር ላይ ያለነው በኑሮም በቃልም የእርሱን በጎነት እንድናገር ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም ነው ብለን ስለእግዚአብሄር በጎነት ለመመስከር በምድር አለን፡፡ እግዚአብሄር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር በሃጢያታችሁ እንድትሞቱ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የመዳኛ መንገድ አዘጋጅቶዋል፡፡ እግዚአብሄር ልጁን ስለሃጢያታችሁ ልኮዋል፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችሁ በመስቀል ላይ ሞቷል ብለን ስለእግዚአብሄር መልካምነት ለመመስከር በምድር ላይ አለን፡፡
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ሐዋርያት 26፡22-23
ይህን በክርስቶስ የመስቀል ስራ በፀጋ የሚዳንበትን ወንጌል ለመመስከር የሰዎችን ተቃውሞ በመጋፈጥ ለሰዎች በድፍረት ወንጌልን መመስከር ይኖርብናል፡፡
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። ሐዋርያት 20፡24
እግዚአብሄር እንደዚህ ይላል ተናገር ዝምም አትበል በዚህ ከተማ የሚድኑ ብዙ ህዝብ አለኝና፡
ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው። ሐዋርያት 18፡9-10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment