Popular Posts

Monday, July 9, 2018

ከሁኔታዎች መጠበቅ ያሰናክላል

መንፈሳዊ አለም አለ፡፡ ተፈጥሮአዊ አለም አለ፡፡ እምነት የሚመሰክረው ስለማይታየው ስለመንፈሳ አለም ነው፡፡
ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ወደ ዕብራውያን 11፡3
ሁኔታ የሚመሰክረው ስለሚታየው ተፈጥሮአዊው አለም ብቻ ነው፡፡ የአካባቢው ሁኔታዎች የራሳቸው ስፍራ አላቸው፡፡ ሁኔታዎች የራሳቸው ድንበር አላቸው፡፡ ሁኔታዎች ማድረግ የሚችሉት ነገር አለ፡፡ ሁኔታዎች ማድረግ የማይችሉት ነገር አለ፡፡ ሁኔታዎች መመስከር የሚችሉት ነገር አለ፡፡ ሁኔታዎች መመስከር የማይችሉት ነገር ደግሞ አለ፡፡ የአካባቢ ሁኔታዎች የሚመሰክሩት ስለተፈጥሮአዊው አለም ብቻ ነው፡፡
የአካባቢው ሁኔታዎች ስለመንፈሳዊው አለም መመስከር አይችሉም፡፡ ሁኔታዎች ስለመንፈሳዊ ነገር እንዲመሰክሩ ከጠበቅን እናዝናለን እንሰናከናለን፡፡
ስለእኛ ማንነት መመስከር የሚችለው መንፈሳዊ አለም ብቻ ነው፡፡ ስለእኛ ደረጃ መናገር የሚችለው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡ ስለእኛ ክብርና ማእረግ ሊመሰክር የሚችለው በክብሩ የፈጠረን እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ስለእኛ ማንነት መናገር የሚችልው በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረን እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
የምናልፍባቸው ሁኔታዎች ስለእኛ ምንነት ሊናገሩ አይችሉም፡፡ የምናልፍበት ሁኔታ ስለእኛ ማንነት ለመናገር አቅሙ አይፈቅድለትም፡፡
ሰዎች ስለሁኔታቸው ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ ምስክርነት ሲፈልጉ ይሳታሉ፡፡ ሰዎች ስለማንነታቸው ሁኔታ እንዲመሰክርላቸው ሲጠብቁ ይሰናከላሉ፡፡ ሰዎች ስለማንነታቸው ሁኔታ እንዲመሰክር ሲጠብቁ ሁሉ ነገር ይዛባባቸዋል፡፡ ሰዎች ሁኔታ ስለማንነታቸው እንዲመሰክር ሲጥሩ ከክብር ይወድቃሉ፡፡
ሰዎች ያላቸው ገንዘብ ስለማንነታቸው እንዲናገር ሲፈልጉ ራሳቸውን ያዋርዳሉሉ፡፡ ሰዎች ስለክብራቸው ዝናቸው እንዲናገርላቸው ሲጠብቁ ከክብር ይወድቃሉ፡፡ ሰዎች ስለማእረጋቸው ሃይላቸው እንዲናገር ሲጠብቁ ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ ሰዎች ስለማንነታቸው እውቀታቸው እንዲናገር ሲፈልጉ ሞኝ ይሆናሉ፡፡
ያለን ገንዘብ ስለማንነታችን ለመመስከር ህፃን ነው፡፡ ያለን እውቀት ስለማንነታችን ለመመስከር አቅሙ አይፈቅድም፡፡ ያለን ሃይል ስለማእረጋችን በትክክል ለመግለፅ አይችልም፡፡ ያለን ዝና ስለማንነታችን ለመግለፅ ህፃን ነው፡፡ የምናልፍበት ሁኔታ ስለማንነታችን ለመመስከር አይችልም፡፡
መመስከር ከማይችሉት ምስክርነት የማንቀበለው ስለዚህ ነው፡፡ መመስከር የማይችለው የሚታየው ሁኔታ እንዲመራን የማንፈቅደው ስለዚህ ነው፡፡ ሊመራን የሚችለው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ እንዲመራን የምንፈቅደው ስለዚህ ነው ፡፡
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡6-7
የማይታየውን የእግዚአብሄርን ቃል እንጂ የሚታየውንም ሁኔታ የማንመለከተው ሁኔተ ትክክለኛውን ምስክርነት ሊሰጥ ስለማይበቃ ነው፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ማየት #መስማት #የሚታየው #የማይታየው #እንመልከት #አንመልከት #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment