Popular Posts

Follow by Email

Saturday, July 28, 2018

ደካማ በድካሙ አይዘን ፥ ደሃ በድህነቱ አይሸማቀቅ ፥ ያልተማረ ባለመማሩ አይዋረድ

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-14
ሰው ምህረትን የሚያገኘው ጠቢብ ስለሆነ አይደለም፡፡ ሰው ለእርሱ ፍርድ የሚፈርድለት ሃያል ስለሆነ አይደለም፡፡ ሰው ፅድቅ የሚሆንለት በባለጠግነቱ አይደለም፡፡
ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ማለት በተቃራኒው ያልተማረ ባለመማሩ አይዋረድ ማለት ነው፡፡ ጠቢብ ጥበቡ ለህይወት ስኬት ብልጫን እንደማይሰጥው ሁሉ ያልተማር አለመማረሩ ከከህይወት ወደኋላምንም አያስቀረውም፡፡ ሃያል በሃይሉ ምንም እንማያመጣ ሁሉ ደካማ ድካሙ ምንም አይጎዳውም፡፡ ባለጠጋው ብልጥግና የህይይወት ቁልፍ እንደማይሰጠው ሁሉ ድሃው ድህነቱ የህይወትን ስኬት ቁልፍ አይከለክለውም፡፡
ሰው በጥበቡ ሊመካ አይገባምን፡፡ ሰው በአለመማሩ ሊሸማቀቅ አይገባም፡፡ ሰው በሃይሉ ደስ ደስ ሊለው አይገባም፡፡ ሰው በድካሙ ማዘን አይገባውም፡፡ ሰው በባለጠግነቱ የህይወት ስኬት ቁልፍ እንዳለው ሊያስብ አይገባም፡፡ ሰው በድህነቱ የተጣለ እንደሆነ ሊያስብ አይገባም፡፡
የሰው ጥበብ ምንም አይጨምርም የሰው አለመማር ምንም አይቀንስም፡፡ የሰው ሃይል ምንም አያመጣም የሰው ድካመ ምንም አይቀንስም፡፡ የሰው ባለጠግነት ብልጫ የለውም የሰው ድህነት የሚቀንሰው ነገር የለም፡፡
የህይወት ስኬት ቁልፍ ጥበብ ውስጥ ፣ ሃይል ውስጥና ባለጠግነት ውስጥ የለም፡፡ የሚያሳካ እግዚአብሄር ብቻ  ነው፡፡ በእውነት የሚያከናውን እግዚአብሄር ነው፡፡ የህይወትን ቁልፍ የያዘው እግዚአብሄር ነው፡፡  
መመካት ያለብን ምሕረትን በሚያደርግ በእግዚአብሄር ነው፡፡ ማንም ሰው በጥበቡ በሃይሉና በብልጥግናው ምህረትን መግዛት አይችልም፡፡ ምህረት ከእግዚአብሄር የሚሰጥ ነፃ ስጦታ ነው፡፡  
ለሙሴ፦ የምምረውን ሁሉ እምረዋለሁ ለምራራለትም ሁሉ እራራለታለሁ ይላልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 9፡15
የሰው ርህራሄ የትም አያደርስም የእግዚአብሄር ርህራሄ ግን የሰውን ህይወት ይለውጣል፡፡
ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። መዝሙረ ዳዊት 63፡3
መመካት ያለብን ፍርድን በሚያደርግ በእግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሄር የሁሉም ዳኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ እግዚአብሄር መማለጃን አይቀበለም፡፡ እግዚአብሄር ቅን ፈራጅ ነው፡፡
እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው፤ የበቀል አምላክ ተገለጠ። የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ከፍ ከፍ በል፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው። መዝሙረ ዳዊት 94፡2-3
መመካት ያለብን ጽድቅን በሚያደርግ በእግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሄር ሁሉንም ያውቃል፡፡ በጥበቡ የሚያታልለው ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄር ፃዲቅ ፈራጅ ነው፡፡  
ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤ ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 11፡3-4
በእግዚአብሄር ፊት ሁሉ ነገር የተገለጠ ነው፡፡
እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ወደ ዕብራውያን 4፡13
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-14
የህይወት ስኬታችን ቁልፉ ባለው በእግዚአብሄር ብቻ ከተመካን መልካም እናደርጋለን፡፡
እግዚአብሄር ሆይ በአንተ እንመካለን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ጥቢብ #ማስተዋል #መረዳት #ሃያል #ባለጠጋ #ኢየሱስ #ጌታ #ደሃ #ያልተማረ #ደካማ #ፅድቅ #ፍርድ #ምህረት #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment