Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, July 18, 2018

ከጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ

ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 4፡17
ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ ያለበት ምክኒያት አለው፡፡ በህይወቱና በአገለግሎቱ ብዙ ሰዎች አገልግሎታቸውን መፈፀም ሲያቅታቸው ተመልክቷል፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ ተጠንቀቅ ያለበት ምክኒያት ማንም ሰው ካልተጠነቀቀ አገልግሎትን ከመፈፀም ሩጫ ሊያቋርጥ እንደሚችል ስለሚረዳ ነው፡፡
ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፤ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡10
አገልግሎት ካለጥንቃቄ የሚፈፅሙት ቀላል ተልእኮ አይደለም፡፡ አገልግሎት ብርቱ ጥንቃቄን ይጠይቃል፡፡ በክርስትና ህይወትና አገልግሎት በተለያየ ምክንያት ወደኋላ መመለስ ያለ በእለት ተእለት ህይወታችን የሚከሰት ነገር ነው፡፡  
ከክርስትና ህይወትና አገልግሎትን በመንፈስ በመጀመር በስጋ ሊጨረስ የሚችልበት እድል ያለበት ጥንቃቄን የሚፈልግ የህይወት ዘመን ሃላፊነት ነው፡፡
እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? ወደ ገላትያ ሰዎች 33
ክርስትና ህይወትና አገልግሎት ጠላት የሚጠላውና በቀጣይነት የሚዋጋው አገልጋዩን ሊውጥ የተዘጋጀበት ልዩ ጥንቃቄን የሚፈልግ የህይወት ሃለፊነት ነው፡፡
በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡8
1.      በራስ ጉልበት ለማገልገል መሞከር
የእግዚአብሄር ስራ የሚሰራው በራሱ በእግዚአብሄር ሃይል ነው፡፡ አገልግሎት ማለት እግዚአብሄር በህይወታችን የሚሰራውን አይተን መከተል መተባበር ማለት ነው፡፡ አገልግሎትን የምናገለግለው ከእግዚአብሄር ጋር አብርን በመስራት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ የምንሰራው እግዚአብሄር ሲሰራ በእምነት በመተባበር ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ የምንሰራው በቦታችን ቆመን ምልክት በመሆን ብቻ ነው፡፡ 
የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡9
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ። ትንቢተ ዘካርያስ 4፡6-7
2.     ከአገልግሎት በሚገኝ ጥቅም ላይ ማተኮር
አገልግሎት የተራቡና የተጠሙ ሰዎች ሳይሆን በእግዚአብሄር አቅርቦት የረኩ ሰዎች ስራ ነው፡፡ ሰው በአገልዕገሎት ሰውን መጥቀም ላይ ሰውን መባረክ ላይ ለሰው በመስጠት ላይ ካላተኮረ ስኬታማ አየሆንም፡፡ ሰው አገልግሎትን ለመጠቀሚያነት ለግል ጥቀም ማካበቻ ከተጠቀመበት ውድቀት ነው፡፡ መንፈሳዊነት ወይም የመጠቀሚያ መንገድ ሳይሆን ራሱ ጥቅም ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማገልገል በራሱ እድል ነው እንጂ ለግል ጥቅም የመጠቀሚያ መንገድ አይደለም፡፡
እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡4-5
መፅሃፍ ቅዱስ ወንጌልን የሚሰራ በወንጌል ይኑር ይላል፡፡ ነገር ግን አገልጋይ ዋናው አላማው ገንዘብና ጥቅም ሲሆን የአገልጋይ ትኩረቱ ገነዘብ ሲሆንና ማናቸውም የሚያደርገውን አገልግሎት ከሚያገኘው ጥቅም ጋር ካመዛዘነ በእውነት ማገልገል አይችልም፡፡
3.     የእግዚአብሄርን መንፈስ አለመጠበቅ፡፡
የእግዚአብሄር ስራ የሚሰራው በመንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚደሰተው በምንፈስ ስለምናገለግለው አገልግሎት ነው፡፡ ከመንፈሱ አርዳታ ውጭ እግዚአብሄርን ለማገልግል መሞከር ከንቱ ልፋት ነው፡፡ ትሁት ሆነን የእግዚአብሄርን መንፈስ ሰምተን እና ጠብቀን የምናገለግለው አገልግሎት ውጤታማ ያደርገናል፡፡
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ዘካርያስ 4፡6
መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡13
4.     የክርስቶስን ሳይሆን የራስን ክብርን መፈለግ
እግዚአብሄር ለአገልጋይ ተሰሚነትንና ክብርን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር ተሰሚነትና ክብር ለአገልጋይ የሚሰጠው ለወንጌል ስራ ነው፡፡ እግዚአብሄር በህዝብ ዘንድ ተሰሚነት ሲሰጠን የእግዚአብሄር መንግስት ሰራተኞች እንደመሆናችን መጠን ለእግዚአብሀረ መንግስት መስፋትና ጥቅም ነው፡፡ ሰው ግን ክብሩን ለራሱ ለግል ጥቅም ሲያውለው መውደቅ ይጀምራል፡፡ አገልጋይ እግዚአብሄር የሰጠንን ተሰሚነትና ሞገስድ ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም ሳይሆን ለራሱ የግል ጥቅም ካዋለውና ወደራሳችን  ካዞርነው እግዚአብሄር ያዝናል፡፡
እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤ ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።  ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡20-21
5.     እግዚአብሄርን ያልመራንን ለማድረግ መድፈር
እግዚአብሄር የሰጠን የአግልገሎት ፀጋ የሚሆነው እርሱ ላዘዘን አላማ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄ ያስታጠቀን ለጠራነ አላማ ብቻ ነው፡፡ ሰው ግን ከከንቱ ውድድርም ተነሳሰቶ እርሱ ካደረገው እኔም ላደርገው እችላለሁ ብሎ እግዚአብሄ ያላዘዘውን ነገር ማድርግ ህይወትን ማባከብን ራስን እና አግህልገሀሎትን መቅጨት ነው፡፡ የእግዚአብሀር አገልጋይ እግዚአብሄር ለምን እንደጠራውና ለምን እነዳልጠራው ካላወቀ ህይወቱን በክንቱ ያባክናል፡፡
ከሕዝቡም አንድ ሰው፦ መምህር ሆይ፥ ርስቱን ከእኔ ጋር እንዲካፈል ለወንድሜ ንገረው አለው። እርሱም፦ አንተ ሰው፥ ፈራጅና አካፋይ በላያችሁ አንድሆን ማን ሾመኝ? አለው። የሉቃስ ወንጌል 12፡13-14
ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና፥ ወንጌልን ልሰብክ እንጂ፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡17
6.     ዝናን መፈለግ
እግዚአብሄር በውስጣችን ያለው አገልግሎት ለብዙዎች እንዲጠቅም ሲፈልግ ዝናና ተሰሚነታችንን ያበዛል፡፡ እግዚአብሄር ዝናና ተሰሚነትን የሚሰጥበት የራሱ ጊዜና መንገድ አለው፡፡ በመሰረቱ ይበዛም ይነስም ዝናና ተሰሚነት የሌለው አገልጋይ የለም፡፡ ነገር ግን  በራሳችን አነሳሽነት እግዚአብሄር ያልሰጠንን ዝናንና ተሰሚነትን ለማሳደግ ከጣርን እንከስራለን፡፡ ለዝናና ተሰሚነት መስራት ራሱን የቻለ ከባድ ስታ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሀትነ በቅንነነት አገልግሎም ለዝናም ሰርቶ አይሆንም፡፡ ሰው ለዝና የሚሰራው እግዚአብሄን ለከሚያገለግለበት አገልግሎት ጊዜና ጉልብት እውቀት ቀንሶ ነው፡፡ እኛ በአግልገሎታችን ላይ እየተጋን  እግዚአብሀር ግን በራሱ ጊዜ እንደወደደ ተሰሚነትና ዝናን ሲሰጠን ውጤቱ ያማረ የሆናል፡፡
ኢየሱስ ዝነኛ ለመሆን ምንም ነገር ሲያደርግ አናይም፡፡ እንዱየተውን ከወፈወሰ በሁወዐላ ለማንብም እነዳትናገሩ ሲል አናየዋለን፡፡ ምክንያቱም ከጊዜው በፊት የመሆነ ዝና ከጥቅሙ ይልቅ ጊዳቱ ስለሚያመዝን ነው፡፡
ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ። ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት። የማርቆስ ወንጌል 7፡35-36
ዝነኝነት የራሱ የሆነ ሸክሞችና ሃላፊነቶች እና ፈተዎች አሉት፡፡ እግዚአብሄር ዝነኛ ሲያደርገን አብሮ ፀጋውን ይሰጠናል፡፡ በራሳችን ዝነኛ ለመሆን ከሞከር አገልግሎታችንን እንዳናገለግል እንቅፋት ይሆናል ሃላፊነቱና ሸክሙን ለመሸከም አቅም ያጥረናል፡፡  
እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፥ ነገር ግን፦ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤   የሉቃስ ወንጌል 5፡14-15
አገልጋይ በአገልገሎት መፅናት ከፈለገ እግዚአብሄር በሰጠው ትንሽ በምትባለው ዝና መርካትና በሚጠቅማቸው ሰዎች ላይ ማተኮር አለብት፡፡ ያለውን ዝናና ተሰሚነት የሚንቅ እና ከፍ ያለ ተሰሚነትን በራሱ ጉልበት ለመፈልግ የሚንጠራራ ሰው በአገልግሎት አይዘልቅም፡፡
ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም። የማቴዎስ ወንጌል 4፡23-24
ዝነኛ መሆን በአገልግሎት ስኬታማነትን አያሳይም፡፡ ብዙም ዝና ሳይኖራቸው ጥቂት ሰዎችን ብቻ እያገለገሉ ህይወታቸውን የሚያሳልፉ እግዚአብሄር ደስ የሚሰኝባቸው ብዙዎች ታማኝ አገልጋዮች አሉ፡፡
7.     የእግዚአብሄርን ነገር መልመድ
ሰው የእግዚአብሄርን ነገር ከለመደው እግዚአብሄርን እንደሚያውቅው ምንም ስለእግዚአብሄር የማያውቀው ነገር እንደሌለ ካሰበ ይከስራል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ቤተክርስትያን ካልፈራ እና በእግዚአብሄር ሰዎች ውስጥ እግዚአብሄርን ማየት ካቆመ አገልግሎቱ አይቀጥልም፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ሰዎችና ለእግዚአብሄር ቤተክርስትያን ያለውን ክብር ካጣ ሰይጣን እግኝቶታል ማለት ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ቤተክርስትያን በምድር ላይ ክርስቶስን የመወከል ትልቅ ስላጣን እነዳላት ሳይሆን እንደ ተራ ሰው ስብስብ ካየ እና ስለእግዚአብሄር ህዝብና ስለ ቤተክርስትያን ክፋትን ከተናገረ በሰይጣን ማታለል ስር ወድቋል ማለት ነው፡፡ ሰው ለክርስቶስ አካል ክብር ከጎደለው የክርስቶስን አካል የምድር ስልጣን ካልተረዳ በሰይጣን እስራት ውስጥ ወድቆዋል፡፡
እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። የማቴዎስ ወንጌል 18፡17
መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ። ወደ ቲቶ 3፡10-11
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጻድቃን #የታመነ #መቀጨት #ፍጥነት #ጥበብ #ድካም #ብርታት #ዝና #ነውር #ስጋ #ዘመን #መውጣት #መውረድ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥቂትበጥቂት #ሙሉቀን #እየተጨመረ #በረከት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment