Popular Posts

Friday, July 6, 2018

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

ክፉን በክፉ ላለመመለስ ህፃናተ ሁኑ እንጂ ስለህይወታችሁ እወቁ፡፡ ህይወታችሁን እንዳመጣላችሁ አትምሩት፡፡ ህይወታቸሁን ለመምራት አስቡ አቅዱ በእግዚአብሄር ቃል የታደሰ አእምሮዋችሁን ተጠቀሙ፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20
መውጫ መግቢያውን የምትቃኙ ንቁዎችና ብልሆች ሁኑ እንጂ ወደ ወሰዷችሁ የምትጎተቱ ሞኞች አትሁኑ፡፡
እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 10፡16
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3
በእእምሮው ህፃን የሆነ ሰው የራሱ የህይወት መርህ የለውም የመጣው ነገር ሁሉ ይወስደዋል፡፡
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡11
እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14
በአእምሮው የበሰለ ሰው የሰው የግል መጠቀሚያ አይሆንም፡፡ በአእምሮ የበሰለ ሰው ዘሎ ውሳኔን አይወስንም በአእመሮ ህፃን ያልሆነ ሰው አካሄድን ይመለከታል ይመዝናል፡፡  
በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡17
የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። መጽሐፈ ምሳሌ 14፡15
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #ህፃንነት #ብስለት #ጥበብ #ማስተዋል #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንድነት #ትህትና #አክብሮት #ስልጣን #መሪ

No comments:

Post a Comment