Popular Posts

Saturday, September 7, 2024

መልካም አዲስ ቤተሰብ


አዲሱን አመት በእውነት አዲስ የሚያደርገው በአዲሱ የእግዚአብሔር በተሰብ ውስጥ መሆናችን ነው። ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ አዳኝ ካልተቀበልን በስተቀር የእግዚአብሔር ልጆች መሆን በፍጹም አንችልም።
እውነት ነው ሰይጣን የፈጠርው አንድም ሰው የለም። ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር ፍጥረት ነው። ሁሉም ግን የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።
በሃጢያት ውድቀት ምክኒያት ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ክብር ጎድለዋል። በሃጢያት ውድቀት ምክኒያት ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ለዘላለም ተለያይቶዋል። ስለዚህ ክርስቶስን የተቀበለ ሰው ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር ፍጥረት ስለሆነ ብቻ  ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይሆንም። 
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። የዮሐንስ ወንጌል 1፥12-13
የእግዚአብሔር ልጅነት ክርስቶስን ለተቀበሉ ሰዎች ብቻ የተሰጠ ስልጣን እንጂ ለሁሉም አይደለም። 
ክርስቶስ ስለ መዳናችን የሃጢያታችን እዳ ሁሉ ከፍሎዋል፤ አሁንም ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፋችን ብንመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልባችን ብናምን ከመቅጽብት እንድናለን።
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።ወደ ሮሜ ሰዎች 10፥9-10
ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የሞተልንን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር በቤተሰብ ውስጥ እንግባ።
መልካም አዲስ ቤተሰብ መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


 

No comments:

Post a Comment