ነገር
ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡7
እግዚአብሄር ትሁት እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር
እንድመካ አይፈልግም፡፡ ሰው የተሰጠውን ስጦታ የራሱ እንደሆነ ከመጀመሪያውም እንደነበረው እንዲያስመስል እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ተቀብሎ እንዳልተቀበለ እንዲመካ እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡
እግዚአብሄር ታላላቅ መዝገቦችን በውስጣችን አስቀምጧል፡፡
የእግዚአብሄር መንፈስ በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡
ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?
በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡19-20
እግዚአብሄር መንፈሱን ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሄር
ቅባትን ሰጥቶናል፡፡ የቀባን እግዚአብሄር ነው፡፡
በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡20-21
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን
የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡20፣27
እግዚአብሄር ስጦታዎችን ሰጥቶናል፡፡
ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤ ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡10-11
እግዚአብሄር የተለያዩ አገልግሎቶችን በእኛ ውስጥ
አስቀምጧል፡፡
እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡11
የእግዚአብሄር
ሃይል ታላቅነት ከእኛ እንዳልሆነ የሚያሳውቀው ታላቁ ሃይል ታላቅ እቃ ውስጥ ስላልተቀመጠ ነው፡፡ ታላቁ ሃይል ታላቅ እቃ ውስጥ
ቢቀመጠ ኖሮ ሰው የሃይሉ ታላቅነት ከእኛ የሆነ ይመስለው ነበር፡፡ ታላቅ መዝገብ በታላቅ እቃ ውስጥ ቢቀመጥ ኖሮ እኛም የሃይሉ
ታላቅነት ከእኛ እንደሆነ ይመስለን ነበር፡፡
ነገር
ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
4፡7
በውስጣችን
ያለው መልካም ነገር ሁሉ የተቀበልነው እንደሆነና የእኛ እንዳልሆነ ግልፅ ምልክት አለው፡፡ በውስጣችን ያለው ይህ መዝገብ ከእኛ
እንዳልሆነ የሚያሳየው መዝገቡ የተቀመጠው በከበረ እቃ ውስጥ ሳይሆን በሸክላ እቃ ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር የከበረውን መዝገብ በእኛ ውስጥ ያስቀመጠው በሚሰበር በሸክላ እቃ ውስጥ ነው፡፡
ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን ምንም ሰው
የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ያውቃል፡፡ ይህ ታላቅ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ስለ አለን እኛም የኃይሉ
ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ከጊዜ ወደጊዜ ያስታውሰናል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ያልታወቁ
#የታወቅን #የምንሞት
#ሕያዋን #የተቀጣን
#አንገደልም
#ኀዘንተኞች #ደስ #ድሆች #ባለጠጎች #የሌለን #ሁሉየእኛነው
#ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል
#የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ
#የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ሰላም
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment