Popular Posts

Thursday, July 5, 2018

እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ

በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ። የያዕቆብ መልእክት 2፡12
በክርስቶስ ከሃጢያት እስራትና ፍርድ ነፃ ወጥተናል፡፡ ነገር ግን ነፃነት የሚመጣው ከሃላፊነት ጋር ነው፡፡ ነፃነት ሃላፊነትን ይጠይቃል፡፡ ሃላፊነትን የማይጠይቅ ነፃነት የለም፡፡
ነፃነትን ለሃጢያት ምክኒያይ ሊሰጥ አይገባውም፡፡ ነፃ በወጣን መጠን ከሃጢያት እየራቅን እንጂ ወደ ሃጢያት መቅረብ የለብንም፡፡ ነፃነታችን ሃጢያትን ላለማድረግ እንጂ ሃጢያትን ለማድረግ አይሁን፡፡  
ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡13
እግዚአብሄር ከጨለማው ስልጣን አድኖናል ወደፍቅሩም ልጅ መንግስትይ አፍልሶናል፡፡ ይህ የፈለስንበት መንግስት ግን ያለ ስርአት አይደለም፡፡ በዚህ መንግስት የማሰብ የመናገርና የማድረግ ስርአት አለ፡፡
እውነት ነው በዚህ መንግስት ስንኖር ተፈርዶበት ወደሲኦል እንደሚጣል ጌታን ኢየሱስን እንዳልተቀበለ ሰው አይፈረድብንም፡፡
ሰው ስለሚናገረው ማንኛውም ከንቱ ነገር ሁሉ መልስ ይሰጥበታል፡፡  
እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ የማቴዎስ ወንጌል 12፡36
ነገር ግን በዚህ መንግስት የሰራነው ስራ ለምን እንደሰራነው መነሻ ሃሳባችን ይፈተናል፡፡
ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡12-15
በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ። የያዕቆብ መልእክት 2፡12
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አክሊል #ፍርድ #ወርቅ #ብር #የከበረድንጋይ #እሳት #ፈተና #ሽልማት #ትንሳኤ #ሰማይ #የማይጠፋአከሊል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment