እንዲሁም፥
ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡5-6
ሰው
ለእግዚአብሄር እንደሚገዛ የሚታወቀው ለሰው ሲገዛ ነው፡፡ እግዚአብሄር
በየደረጃው በህይወታችን ላይ ያስቀመጣቸው ባለስልጣኖች አሉ፡፡ እግዚአብሄር ከእናትና አባት ጀምሮ እስከ መንግስት ባለስልጣናት ድረስ
እንዲመሩን ባለስልጣኖችን በህይወታችን ላይ አስቀምጧል፡፡
እግዚአብሄር
በየደረጃው ያስቀመጣቸውን ባልስልጣናት መቃወም የእግዚአብሄርን ስርአት መቃወም ነው፡፡ እግዚአብሄር በየደረጃው በቤተሰብ በቤተክርስትያን
በስራ ቦታ በህይወታችን ላይ ያስቀመጣቸውን ሰዎች መቃወም እግዚአብሄርን መቃወም ነው፡፡ እግዚአብሄር ከቤተሰብ እስከ መንግስትና
ቤተክርስትያን በህይወታችን ላይ የሾማቸውን ባለ ስልጣናት ያለመታዘዝ ችግር እግዚአብሄርን ያለመታዘዝ ችግር ነው፡፡ እግዚአብሄር
ከቤተሰብ እስከ ቤተክርስትያን በእኛ ላይ ያስቀመጣቸውን ባለስልጣናት አለማክበር እግዚአብሄርን አለማክበር ነው፡፡ እግዚአብሄር በየደረጃው
ከቤት እስከ መንግስት በእኛ ላይ በየደረጃው ያስቀመጣቸውን መሪዎች መናቅ እግዚአብሄርን መናቅ ነው፡፡
ነፍስ
ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ
ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ወደ ሮሜ
ሰዎች 13፡1-2
ሰው
የእግዚአብሄርን ስልጣን እንደሚያከብር የሚታየው እግዚአብሄር በህይወቱ ያስቀመጣቸውን ባለስልጣናት በማክበሩ ነው፡፡ ያየውን ሰውን
ያላከበረ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊያከብር እንዴት ይችላል?
ያየውን
ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡20
የሰው
የስልጣን አለማክበር የሚጀምረው የሰውን ስልጣን ባለ ማክበት አይደለም፡፡ የሰው የሰውን ስልጣን አለማክበት የሚጀምረው የሰው የእግዚአብሄር
ስልጣን ባለ ማክበት ነው፡፡ የሰው የእግዚአብሄርን ስልጣን አለማክበር ምልክቱ የሰው የሰውን ስልጣን አለማክበር ነው፡፡
ሰው
አመፅን በቤተክርስትያን ሽማግሌዎች ወይም በሌሎች ባለስልጣኖች ላይ በማመፅ አይጀምርም፡፡ ሰው አመፅን የሚጀምረው በእግዚአብሄር ላይ በማመፅ ነው፡፡ የሰው ለቤተክርስተያን ሽማግሌዎች አለመገዛት ችግር ለእግዚአብሄር አለመገዛት
ችግር ነፀብራቅ ነው፡፡ የሰው ለቤተክርስትያን መሪዎች አለመገዛት ችግር መፍትሄ የሚያገኘው የሰው ለእግዚአብሄር የመገዛት ችግር
ሲፈታ ነው፡፡
ስለዚህ
ነው መፅሃፍ ቅዱስ ለሽማግሌዎች ተገዙ ካለ በኋላ ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ የሚለው፡፡ ከእግዚአብሔር እጅ በታች
ራሱን ያዋረደ ሰው ለሽማግሌዎች መገዛት ይችላል፡፡ ከእግዚአብሔር እጅ በታች ማዋረድ ራሱን ያስለመደ ሰው ለሽማግሌዎች መገዛት አይከብደውም፡፡
ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሱን ያላዋረደ ሰው ግን ለሽማግሌዎች መገዛት አይችልም፡፡ የሰው ለሽማግሌዎች የመገዛት ችግር የሚፈታው
የሰው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሱን የማዋረድ ችግሩ ሲፈታ ብቻ ነው፡፡
እንዲሁም፥
ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን
ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን
አዋርዱ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡5-6
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ትህትና #መዋረድ #መገዛት #ሽማግሌ #ባለስልጣን #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment