ዳሩ
ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። 1ኛ
የጴጥሮስ መልእክት 1፡15-16
በእርሱም
ይህን ተስፋ የሚያደርግ እርሱ እንደማይቀላቀል ራሱን አያቀላቅልም፡፡ በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ርኵስንም አይነካም፡፡
ስለዚህም
ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት
እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17-18
በእርሱም
ይህን ተስፋ የሚያደርግ ራሱን ከአለም እድፈት ይጠብቃል፡፡
አንደበቱን
ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው። ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ . . . በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው። የያዕቆብ መልእክት 1፡26-27
በእርሱም
ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡3
በትልቅም
ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡20-21
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ቅዱስ #ክፉ #ቅድስና #እርኩሰት #የተቀደሰ
#ለክብር #ለውርደት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ተስፋ #ያነፃል #ክብር #ውርደት
No comments:
Post a Comment