ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። የሐዋርያት ሥራ 16:30
ይህ የብዙ ሰው የልብ ጨኸት ነው፡፡
ይህ በህይወት ዘመን ሊመለስ የሚገባው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡
ይህ የእውቀት ጥያቄ አይደለም፡፡ ይህ የጥበብ ጥያቄ አይደለም፡፡ የህ የህግይወትና የሞት ጥያቄ ነው፡፡
ይህን ጥያቄ በትክክል መመለሳችን ወይም አለመመለሳችን ለዘላለም ከእግዚአብሄር እንድንለይ ወይም ከእግዚአብሄር ጋር እንድንኖር
ያስችለናል፡፡
ይህን ጥያቄ በትክክል መመለሳችን የተፈጠረንበትን አላማ እንድናገኝ እና የተፈጠርንበትን አላማ ባለመሳት ከንቱ እንዳንሆን
ያደርገናል፡፡
ለመዳን መልሱ አጭርና ግልጭ ነው፡፡
እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት። የሐዋርያት ሥራ 16:31
ምክኒያቱም ከክርስቶስ ውጭ መዳን በሌላ በማንም የለም፡፡
መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋርያት
ሥራ 4፡12
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ
የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት
#አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment