ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ
5፡16-18
በህይወት
ማሸነፍ እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ ሰው በህይወቱ ሁል ጊዜ ካለማቋረጥ ማሸነፍ ይችላል፡፡
እኛ
የእግዚአብሄር የክብሩ መገለጫ እቃዎች ነን፡፡ በራሳችን ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ እግዚአብሄር ላይ በታመንን መጠን ሁሉ ግን ሁሌ
እናሸንፋለን የሚሳነንም ነገር አይኖርም፡፡
ሳታቋርጡ
ድል እንድታደርጉ ሳታቋርጡ ጸልዩ፡፡
መፀለይና
ማሸነፍ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሁሌ ማሸነፍ ይቻላል? አንዳንድ ሰዎች ይህ ሊደረስበት የማይቻል ነገር እንደሆነ ያስቡታል፡፡
መልሱ
ግን አዎን ሳያቋርጡ በመፀለይ ሁሌ ማሸነፍ ይቻላል ነው፡፡ ማረጋገጫው
ምንድነው ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ሁሉ መልሱ እግዚአብሄር የማይቻል ነገር አያዝዝም ፡፡ እግዚአብሄር ካዘዘ ይቻላል ማለት ነው ፡፡
ሳያቋርጡ
መፀለይ ማለት ሁሌ ተንበርክኮ መፀለይ ማለት ግን አይደለም፡፡ መፀለይ መንበርከክን ወይም በርን መዝጋትን ቢያጠቃልልም በእነዚህ
ብቻ አይወሰንም፡፡
ሳያቋርጡ
መፀለይ ማለት ካለማቋረጥ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ፣ ካለማቋረጥ ልብን ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ማንሳት እና ሌላም ስራ እየሰሩም
ቢሆን ካለማቋረጥ በውስጥ ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ማለት ነው፡፡ ፀሎት በውስጥ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር መጮኽ ነው፡፡
እግዚአብሄር
የልብን ጩኸት ይሰማል፡፡
እግዚአብሄር
አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ሁሌ እንዲሳካልን ስለሚፈልግ ሳታቋርጡ ጸልዩ እያለ እየጋበዘን ነው፡፡
ሳናቋርጥ
በመፀለይ ሳናቋርጥ እንከናወን፡፡
ይህን ፅሁፍ
ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #የእግዚአብሄርእርዳታ #የልብጩኸት #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment