Popular Posts

Monday, July 18, 2016

በላይ ያለውን እሹ

ከክርስቶስ ጋር በትንሳኤ በመነሳታችንና በሰማያዊ ስፍራ ከክርስቶስ ጋር በመቀመጣችን እንዲሁም በሰማያዊው በረከት ሁሉ ከመባረካችን የተነሳ ሰዎች የሚጋደሉለት የምድር ነገር አያጓጓንም ፡፡
ለጊዜያዊ ደስታ ብለን አባታችንን እግዚአብሄርን ማሳዘን አንፈልግም፡፡ ለምድራዊ ተራ ነገር እግዚአብሄን መፍራታችንን አንተውም፡፡ 
 
ለምድራዊ ክብር ለማግኘት ሰዎችን አንጠላም አንበድልም ፡፡ ለከንቱ የምድር ውድድር የተሰጠንን የክርስትና ወንጌል ተልዕኮ ቸል አንልም፡፡ 
 
ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡32 እንደሚሉ ሰዎች ምድራዊ የሚያልፍ ገንዘብ ለማግኘት ሰዎችን አንቀማም፡፡ 
 
ይህ የእግዚአብሄር ቤተሰብነት የልጅነት ክብራችን አይፈቅድልንም፡፡ ክርስቶስን ለማወቅና ለእርሱና ለእርሱ ብቻ ለመኖር ሁሉን እንደ ጉድፍ እንቆጥራለን፡፡ 
 
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ! 
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

No comments:

Post a Comment