Popular Posts

Wednesday, July 27, 2016

በምድር ተቀመጥ


በምድር ስንኖር የእግዚአብሄርን ፈቃድ በምድር እንዳንፈፅም ሊያስፈሩን የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

አንዳንድ ሰው ወጥቶ ህይወትን መጋፈጥ ሲፈራ ተኝቶ መዋል ያምረዋል፡፡ ሌላው ደግሞ ቶሎ ወደ ሰማይ እንዲሄድ ይመኛል፡፡ የሆነ ቦታ ብቻ መሄድ ከምድር መውጣት ይፈልጋል፡፡

በጌታ በእየሱስ ያመነ ሰው ወደሰማይ የሚሄድበት ጊዜ አለው፡፡ ላሁን ግን የሚሰራ ስራ ስላለ በዚሁ በምድር ይቆያል፡፡

አንዳንዴ የሰዎችን ክፋት ስናይ ዘመኑ ያስፈራራናል፡፡ የፍርሃቱን ስሜት ከሰማነው ሽምድምድ አድርጎ ሊያስቀምጠን ነው የሚመጣው፡፡

የኑሮውን ውድነት ስታስብ እንዴት ነው የሚኖረው ትል ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄር አምላካዊ መልስ ግን ይህ ሁሉ ችግሮች ባሉባት በዚችሁ ምድር ተቀመጥ ታምነህ ተሰማራ ነው፡፡

እግዚአብሄር ግን የሚፈልገው በዚህ በእንግድነት አገራችን በምድር ላይ ታምነን እንድኖር ነው፡፡

እዚሁ ጠላት ባለበት ምድር ላይ ኖረህ እንድታሸነፍ ነው እንጂ  ጌታ ከአለም እንድትወጣ አይደለም የሚፈልገው፡፡

እግዚአብሄርን ከማመናችን በፊት ምድር እየተሻሻለች መሄድ የለባትም፡፡ ከማሸነፋችን በፊት የሰዎች ባህሪ መሻሻል የለበት፡፡ እንዲሳካልን ሰዎች ሁሉ በእግዚአበሄር ማመን የለባቸውም፡፡

አለም ግን ወዴት እየሄደች ነው ብለን በሞራል መላሸቅ መገረማችንን እያለ እንዲያውም እየበዛ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡፡

በእግዚአብሔር ታመን፥ . . . በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ ነው የሚለው፡፡

·        እዚሁ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማ አህዛብን በሚሸፍንበት ነው ብርሃንህን ሊያወጣ የሚፈልገው፡፡

ብርሃን መቷልና የእግዚአብሄርም ክብር መቷልና ተነሽ አብሪ። እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማ አህዛብን ይሸፍናሉ ነገር ግን በአንች ላይ እግዚአብሄር ይወጣል ክብሩም በአንች ላይ ይታያል፡፡ መዝሙር 60፡1-2

·        በሞት ጥላ መካከል ነው አብሮህ መሆን የሚፈልገው፡፡

በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። መዝሙር 23፡4

·        በጠላቶችህ ፊት ለፊት ነው ራስህን በዘይት መቀባት የሚፈልገው፡፡

በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። መዝሙር 23፡5

·        እዚሁ ደረቁ ምድር ላይ መቶ እጥፍ እንድታፈራ የሚፈልገው፡፡

ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው። ዘፍጥረት 26፡12

እግዚአብሄር ግን ታምነን እንድኖር ነው የሚፈልገው፡፡ ለዚህ ነው በምድር ተቀመጥ ታምነህ ተሰማራ የሚለው፡፡

በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። መዝሙር 37፡3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ


#ድፍረት #መተማመን  #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment