Popular Posts

Monday, July 18, 2016

እንደ ሌባ



እየሱስ የሰው ልጆች ሰለ ደህንታቸው ምን እንዳደረጉ ሊጠይቅና በምድር ላይ ሊፈርድ ተመልሶ የሚመጣው እንደሌባ ድንገት ነው፡፡ ሰዎች የእለት ተእለት ኑሯቸውን እየኖሩ እየበሉ እየጠጡ እያገቡና እየተጋቡ ማንም ሳያውቅ ኢየሱስ በድንገት ይመጣል፡፡ 

ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። 1 ተሰሎንቄ 5፡1-2
እየሱስ በቶሎ እንደሚመጣ እንጂ በምን ቀንና ሰአት እንደሚመጣ አናውቅም፡፡ ማድረግ የምንችለው የተሻለ ነገር ተዘጋጅቶ መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ 

የእግዚአብሄር ሰው ማርቲን ሉተር ክርስቶስ ትናንትና እንደሞ ፡ ዛሬ ጠዋት እንደተነሳ ፡ ነገ ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ በዝግጅት ኑሩ በማለት ይመክራሉ፡፡ 

ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ማቴዎስ 24፡36-39

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ! 

No comments:

Post a Comment