Popular Posts

Monday, July 4, 2016

ልጅነቴ

ትዝ ይለኛል ልጆች ሆነን በወላጆቻችን ወደ ሱቅ ወይም ወደ ማደያ እንላክ ነበር ፡፡ ከመካከላችን ለፈጣንና አስተማማኝ መልክት የሚላክ ታማኝ ልጅ አለ ለዚያ የማይላክ የማይታመንበት ልጅ ደግሞ ነበር፡፡ 
 
የወላጆችን የልብ የሚያደርስ መልክተኛ የሚባለው በመንገድ ያለው ወሬ የማይወስደው ፡ አላፊውንና አግዳሚውን ሰውና መኪና ሲያይ የማይቆም ፡ የሆነ ግር ግር ሲያይ ለወሬ የማይጓጓ ሲሆን ልብ የሚያደርስ መልክተኛ ተብሎ በወላጅ ይላካል፡፡ ይህ መልክተኛ የወላጅን ሸክም ተሸክሞ እስከሚፈፅመው የማያርፍ ተወዳጅ መልክተኛ ነው፡፡ 
 
የማይላከው ልጅ ደግሞ ፈጠን ፈጠን ብሎ የማይራመድ ፡ ጉልበቱን የሚሰስት ፡ ወሬ ወይም በመንገድ ላይ የሚያየው ጫወታ የሚያታልለው ፡ እንደተላከ የሚረሳው ፡ አንዳንዴ የተላከውን ረስቶ ሌላ ነገር ገዝቶ የሚመጣ ወይም ደግሞ ከተላከ እጅግ ዘግይቶ የሚደርስ ልጅ ነው፡፡
 
አሁንም እኛ በምድር ላይ ያለነው በእግዚአብሄር ተልከን ነው ፡፡ (2ኛ ቆሮንጦስ 5፡20) ይህ ቤታችን አይደለም፡፡ /(ፊልጵስዩስ 3፡20) በምድር ያለነው መብላትና መጠጣት ትልቅ ነገር ሆኖ ሳይሆን ለስራና ለተልኮ ነው ፡፡ (ዮሃንስ 20፡21) 
 
ስለዚህ በልጅነታችን የልብን እንደሚያደርሰው ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤(ማቴዎስ 25፡21) የሚለው ልጅ እንሁን 
 
የአለም ብርሃንና የምድር ጨው የመሆን መልክታችንን ለአፍታ ረስተን በዚያ ፋንታ ሌላ ነገር ስናደርግ አንገኝ (ማቴዎስ 5፡14) 
 
በምድር ያለው ክፉ ውድድር ሳያጓጓን "የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል" የተላክንበትንም የወንጌል አላማ ፈፅመን የላከንን ጌታ እናስደስት (ማቴዎስ 13፡22) 
 
በሃጢያት ሃሳብና በነፍስ ተግዳሮት መልክተኞች መሆናችንን በሰማይ የሚጠብቀንና የሚጠይቀን የላከን እንዳለ አንርሳ (1ኛ ጴጥሮስ 2፡11) 
 
እንደ ሰነፉ ልጅ ለጌታ ስራ ጉልበታችንን ጊዜያችንን ገንዘባችንን ሳንሰስት ለጌታ ኖረን እንለፍ (ሉቃስ 6፡38) 
 

No comments:

Post a Comment