Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, July 6, 2016

የክህደት ጥሪ

ክርስቲያን መሆን ወይም የእየሱስ ተከታይ መሆን የሃይማኖት ለውጥ ማድረግ አይደለም፡፡ የእየሱስ ደቀመዝሙርነት ጥሪ የሃይማኖት ለውጥ ጥሪ አይደለም፡፡ ክርስትና ራስን የመካድ ጥሪ ነው፡፡

ሌሎች ሃይማኖቶች የተለያየ ደንብና ስርአት ይቀበላሉ፡፡ ክርስትና ግን ራስን ከመካድ ያነሰ ነገር አይቀበልም፡፡ ሰው ምንም ያህል መልካም ምግባር ለማድረግ ቢሞክር ራሱን ክዶ እየሱስን ካልተከተለ ደቀመዝሙር ሊሆን በፍፁም አይችልም፡፡

ለሁሉም እንዲህ አላቸው። በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ። ሉቃስ 9፡23

እየሱስ ስለ ሃጢያታችን እንደሞተ እኛ ደግሞ የነፍሳችንን የሃጢያት ምኞት ክደን ለእርሱ ልንኖርለት ይገባል፡፡ እለት በእለት በቃሉ የመኖር ሃላፊነታችንን እየተወጣን ለእርሱ እና ለእርሱ ብቻ እንድንኖርለት ይፈልጋል፡፡

ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

No comments:

Post a Comment