Popular Posts

Thursday, July 14, 2016

ምን ይጠቅማል ?



ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16:26 

ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ማለት በአለም ላይ ያለው ሀብት ሁሉ የእርሱ ቢሆን ፡ በአለም አንደኛ ዝነኛ ቢሆን ፡ በአለም ላይ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ለማድረግ የሚችል ሃያል ሰው ቢሆን ማለት ነው፡፡ ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? 

መልሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡ 

ከነፍስ  ዋጋ ጋር ሲተያዩ እነዚህ ነገሮች ከንቱ የከንቱም ከንቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ተደምረውና ከአንድ ነፍስ ጋር በፍፁም አይወዳደሩም፡፡  

ሰው እነዚህን ሃብት ፡ ዝናና ፡ ሃይል ሁሉ ደምሮ ለነፍሱ ቤዛና ዋጋ ሊከፍልላት የማይበቁ እጅግ በጣም ጥቂት ነገሮች ናቸው፡፡ 

በምድር ላይ እነዚህን ነገሮች ብናጣ በአለም ላይ ማንም ባያውቀን ፡ የመጨረሻ ደካማ ሰዎች ብንሆን ፡ ከምንበላውና ከምንለብሰው ውጭ ምንም የሌለን ብንሆን እንኳን ነፍሳችንን ካላጣን አንጎድልም አንከስርም፡፡ ነፍሳችንን ላለማጉደል እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንኳን ብንተው ተጠቃሚ ነን አትራፊም ነን፡፡ 

ነፍሳችንን ላለማጉደል የምንወስደው ማንኛውም እርምጃ ሁሉ ትክክለኛ የጠቢብ ውሳኔ ነው፡፡ 

ስለዚህ ነው ከመርፈዱ በፊት ጌታ እየሱስን ለመከተል መወሰን ያለብን፡፡ 

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16: 24-26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ! 

No comments:

Post a Comment