በታሪክ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ ተጠቃሚዎቹ ስለነዳጅ ፍጆታቸው በደንብ ማሰብ ጀመሩ፡፡ ከዚያም የነዳጅ ፍጀጆታቸውን ካልቀነሱ እየጨመረ ያለውን የነዳጅ ዋጋ መቋቋም እንደማይችሉ በተገነዘቡ ጊዜ እርምጃዎችን ወሰዱ፡፡ ከወሰዱዋቸው እርምጃዎች መካከል አንድ መኪና በምን ያህል ፍጥነት ሲጓዝ ዝቅተኛ ነዳጅ እንደሚበላ ማጥናትና መተግበር አንዱ ነበር፡
ሁለተኛ በመርከቦችና በመኪናዎች ላይ ያሉ ከባድ ግን አላስፈላጊ የሆኑ ሸክሞችን አስወገዱ፡፡ በዚህ ሁኔታ የነዳጅ አጠቃቀማቸውን በመቀነሳቸው በነዳጅ ላይ ያላቸውን መደገፍ መቀነስና ህይወታቸውን ቀለል ማድረግ ችለው ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ የነዳጅ ሻጮቹ የነዳጁን ዋጋ እንዲቀንሱ ማስገደድ ችለው ነበር፡፡ እስከያ ጊዜ ግን ባነሰ ነዳጅ መኖር እንደሚቻል አይረዱም ነበር፡፡
በህይወት ዘመናችን የምንፈልገውንና የሚያስፈልገንን መለየት አንድ ሲደመር አንድ ስንት ይሆናል እንደሚለው ቀላል አይደለም፡፡
በህይወታችን የሚያስፈልገን ነው ብለን በሙሉ ልባችን የምናምነው ነገር ሁሉ ላያስፈልገን ይችላል፡፡ በእውነት የማያስፈልገን መሆኑን የምንረዳው አጥተነው ካለ እርሱ በስኬት መኖር ስንችል ነው፡፡
አሁንም የምንፈልገው ነገር ላይ ሳይሆን የሚያስፈልገን ነገር ላይ ብቻ ካላተኮርን ለእግዚአብሄር የመኖራችን ውጤታማነት ይቀንሳል፡፡ የኑሮ ጥያቄ አያልቅም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል ባልንበት መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የምንችለው፡፡
አሁንም እኛ መለወጥ እንችላለን፡፡ ከምናስበው በላይ ካለብዙ ነገሮች መኖር ማሸነፍ መከናወን እንችላለን፡፡ ካልሆነ ግን ራስን ሳያማጥኑ ለእግዚአብሄር መኖርም ሆነ እግዚአብሄርን ማገልገል ዘበት ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
No comments:
Post a Comment