እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። ናሆም 1፡7
እግዚአብሄር መልካም ብቻ ሳይሆን የማይለወጥ ወረት የማያውቀው ሁል ጊዜ መልካም ነው፡፡
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያዕቆብ 1፡17
እንዲያውም የመልካምነትን ትርጉም በትክክል የምናውቀውና የምንረዳው በእግዚአብሄር ነው፡፡ ስለ መልካምነት ክርክር ከተነሳ ክርክሩን ካለማወላወል ሊፈታ የሚያስችለው እግዚአብሄርን ማየት ነው፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር የኖሩ ሰዎች በብዙ ከፍታና ዝቅታ ውስጥ አልፈዋል ሁሉም ግን ሲወጡ የሚሉት "እግዚአብሄር መልካም ነው" ነው፡፡
ስለዚህ ነው እግዚአብሄርን ማመስገን ምንም የሚወጣለት ነገር የሌለው፡፡ ሰው ቢሳሳት ቢሳሳት እግዚአብሄርን በማመስገን አይሳሳትም ምክኒያቱም እግዚአብሄር መልካም ነውና፡፡
እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። መዝሙር 136፡1
እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፡፡ መዝሙር 135፡3
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
No comments:
Post a Comment