Popular Posts

Friday, July 22, 2016

ታላቅ ነው !

ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ኛ ዮሐንስ 4:4
በክርስትና ህይወታችን የትም አትሄድም ፣ በላሁህ ፣ ጣልኩህ ፣ አሁንስ አታመልጥም ብለው የሚያስፈራሩ ብዙ ነገሮች ይነሳሉ፡፡ በአካባቢያችን ያሉትን ሁኔታዎች በማሳየት እግዚአብሄር የተናገረን ነገር እንደማይሆንና ሊፈፀም እንደማይችል ሊያስረዱንና ሊያሳምኑን ይጥራሉ፡፡
ክርስትናን በሚገባ ለመኖር አቅም እንደሌለን የአለም ሃይል እንደሚያሸንፈን በብዙ ሊያሳምኑን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
ነገር ግን . . .
እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ሊቋቋም የሚችል ምንም ሃይል አልነበረም የለም ወደፊትም አይኖርም፡፡ እየሱስ በምድር ሲኖር አሸንፎ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በሙላት እንደፈፀመ እኛንም ሊያሸንፈን የሚችል በፊታችን የሚቆም ምንም ሃይል የለም፡፡
በምድር ያለው ተግዳሮት እንደማናሸንፍ ማረጋገጫ ሊሆን በፍፁም አይችልም፡፡ እንዲያውም የተግዳሮት መኖር ወደአሸናፊነት እየገሰገስን እንደሆንንና ልናሸንፍ እንደምንችል ማረጋገጫው ነው፡፡
ከእኛ የተነሳ ሳይሆን በውስጣችን ካለው የተነሳ እንደምናሸንፍ ሳይታለም የተፈታ ነገር ነው፡፡
በእኛ ያለው በአለም ካለው ማንኛውም ተግዳሮትና ሃይል ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉ

No comments:

Post a Comment