Popular Posts

Saturday, July 23, 2016

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ

የእግዚአብሄርን ፈቃድ መረዳት የመሰለ ነገር የለም፡፡የህይወታችን ጥማት ጌታን መከተልና እግዚአብሄርን ማስደሰት በመሆኑ የእግዚአብሄር ፈቃድን ስናገኝ እንደሰታለን፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነ ነው፡፡ ሮሜ 12፡2
 
ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ የሚለው የእግዚአብሄ ፈቃድ በመፅሃፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ ግልፅ ተደርጎ ተፅፎዋል፡፡ 
 
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
 
እውነት ነው ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ የሚለው ትእዛዝ ሁል ጊዜ ቀላል አይደለም፡፡ ቤጌታ ግን ሁል ጊዜ ደስ መሰኘት ይቻላል፡፡ ግን እንዴትና በምን ምክኒያት ነው ሁል ጊዜ በጌታ ደስ መሰኘት የሚቻለው?
ሁልጊዜ ደስ መሰኘት የሚቻለው እግዚአብሄር በታላቅ ዋጋ የገዛን የህይወታችን ባለቤት መሆኑን በማመን ነው፡፡ እግዚአብሄር ባለቤት ስለሆነ ደግሞ እኛ እንኳን ግድ ባይለን ስለ እያንዳንዱ የህይወታችን አቅጣጫ ዝርዝር ጉዳይ ግድ ይለዋል፡፡ 
 
በዋጋ ተገዝታችኋልና . . . ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20
 
ሁልጊዜ መደሰት የሚቻለው እግዚአብሄር በአላማ እንደወለደን ስንረዳና ኢየሱስን ለሃጢያታችን እስኪሰዋ ድረስ ለእግዚአብሄር በጣም አስፈላጊ ሰዎች እንደ ሆንን ስናስታወስ ነው፡፡ ፍቅር የሆነው እግዚአብሄር ወዶናል፡፡ 
 
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ 1ኛ ዮሐንስ 3፡16
 
ሁልጊዜ በእግዚአብሄር የምንደሰተው እርሱ እረኛችን ስለሆነና በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብናልፍ እርሱ ከእኛ ጋር ስለሚሆን ነው፡፡ 
 
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥. . . በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፡፡ መዝሙር 23፡1፣4
 
ሁል ጊዜ በጌታ ደስ የሚለን ለእኛ የሚያስባትን ሃሳብ እርሱ ስለሚያውቀው ነው፡፡ የህይወት እቅዳችን እርሱ ጋር ስላለና በጥንቃቄም እየፈፀመው ስለሆነ ነው፡፡ 
 
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11
 
ሁልጊዜ ደስ የሚለን ለእኛ የሚያስብልን የተባለ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ አባት በሰማይ ስላለን ነው፡፡ 
 
እርሱ ስለእናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 5:7
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ 
 

No comments:

Post a Comment