ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም። መዝሙር 14፡1
ሰነፍ ወይም ሞኝ እግዚአብሄር የለም የሚለው በቃሉ
አይደለም ፡፡ በቃሉ አውጥቶ ሲናገር ላይሰማ ይችላል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ ጮክ ብሎ እግዚአብሄር የለም ይላል፡፡
ሰው በልቡ እግዚአብሄር የለም ማለቱን ስንፍናውን
የሚያሳዩ ድርጊቶች አሉ፡፡
ሰው እግዚአብሄን መፈለግ ትቶ የእርሱ የህይወት
ቁልፍ በምድር ላይ እንዳለ የሚያስብ ከሆነ በአኳሃኑ እግዚአብሄር የለም እያለ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ፈጥሮት እርሱን የማይፈልግና
የሚገባውን ክብር የማይሰጥ ሰው ሞኝና ሰነፍ ሰው ነው፡፡
እግዚአብሄር እንደሌለ አድርጎ ለእግዚአብሄር ትኩረት የማይሰጥ ሰው ሞኝ
ነው፡፡ በህይወቱ ለእግዚአብሄር ስፍራ የሌለው ሰው የማያስተውል ሰው ነው፡፡
ሰው ብልጠቱና አስተዋይነቱ የሚታወቀው የፈጠረውን
እግዚአብሄርን ሲፈልግ ነው፡፡ የፈጠረውን እግዚአብሄርን ቸል ከማለት በላይ ሞኝነትና ስንፍና የለም፡፡
ሰነፍ በልቡ። አምላክ
የለም ይላል።
ረከሱ በበደላቸውም
ጐሰቈሉ በጎ
ነገርን የሚያደርጋት
የለም። የሚያስተውል
እግዚአብሔርንም የሚፈልግ
እንዳለ ያይ
ዘንድ እግዚአብሔር
ከሰማይ የሰው
ልጆችን ተመለከተ።
መዝሙር 53፡1-2
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
No comments:
Post a Comment