ካለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ እንዲያው ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን ይገባዋል፡፡ ዕብራውያን 11፡6
በአጭሩ ከእግዚአብሄር ለመቀበል እመነት ወሳኝ ነው፡፡
ካለእምነት የእገዚአብሄር ሃይልና በረከት ተጠቃሚ መሆን አይቻልም፡፡
መልካሙ የምስራች ግን እምነት እመነት ይመጣል፡፡ እምነትን ማምጣት ይቻላል፡፡ እምነት ሊኖረን ይችዐላል፡፡ እምነት ልናገኝ እንችላለን፡፡
እምነት ሊመጣ መቻሉ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው ?
ግን እምነት የምናገኘው እንዴት ነው ? እምነት እንዴት የመጣል ?
መፅሃፍ ቅዱስ እምነት እንዲኖረን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን እምነት እንዴት እንደሚመጣም ያስተምረናል፡፡
እምነት ከመስማት ነው መስማትምን በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ሮሜ 10፡17
እምነት የሚመጣበት አንዱና ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሄር ቃል በመስማት ነው፡፡ እምነት የሚመጣበት ሌላ መንገድ የለውም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ከእግዚአብሄር ለመቀበል የሚያስችለን እምነት የሚመጣበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡
በህይወታችን እምነት እንዲበዛና ከእግዚአብሄር አብልጠን ዋጋን እንድንቀበል የእግዚአብሄር ቃል በትጋት እናንብብ እንስማ፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
No comments:
Post a Comment